Tuesday, October 7, 2014

ኢትዮጵያ የአፍሪካ እጅ ኳስ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርን ልታስተናግድ ነው

 
  አለም አቀፉ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ 2015ቱን የአፍሪካ እጅ ኳስ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር እንድታስተናግድ ዕድሉን ሰጣት። ከጥር 16 እስከ 23 ቀን 2007 . ድረስ በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ በሚካሄደው ውድድር 10 የአፍሪካ አገራት ይሳተፋሉ።
   
  የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው፥ አለም አቀፉ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ ውድድሩን እንድታስተናግድ ጠይቋል። የፌዴሬሽኑ ዳይሬክተር አቶ ሰማኸኝ ውቡ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ ከወር በፊት አለም አቀፉ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን ሙሉ ወጪውን የሸፈነውን የዞን አምስት "" የእጅ ኳስ ውድድር በሚገባ ማስተናገዷና ምቹ የስፖርት ማዘውተሪያ መኖሩ እድሉን ለማግኘት አስችሏታል።

  የውድድሩን ሙሉ ወጪ አለም አቀፉ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን እንደሚሸፍንና ከኢትዮጵያ የሚጠበቀው ውድድሩን በተሳካ ሁኔታ ማስተናገድ ብቻ መሆኑንም ነው የተናገሩት። ፌዴሬሽኑ ታዳጊ አገራትን ለማበረታታት መሰል እድሎችን የሚፈጥር ሲሆን፥ ኢትዮጵያም  ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ከውድድሩ ታገኛለች ብለዋል አቶ ሰማኸኝ።

  ኢትዮጵያ ከዞን አምስት "" ሞዛምቢክ ከዞን አምስት"" እና ማዳጋስካር ከዞን ሰባት በሁለቱም ጾታዎች የዞን ውድድሮች ሻምፒዮና የነበሩ ሲሆኑ በዚህ ውድድር ላይም በሁለቱም ጾታዎች ይካፈላሉ። ኬፕቬርዴ በወንዶችና ሴኔጋል በሴቶች ከዞን ሁለት፣ ሴኔጋል በወንዶችና ቡርኪናፋሶ በሴቶች ከዞን ሶስት፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በወንዶችና ቻድ በሴቶች ከዞን አራት እንዲሁም ኡጋንዳ በወንዶችና ኬኒያ በሴቶች ከዞን አምስት "" ተካፋይ ይሆናሉ።

 በውድድሩ  ዕድሜያቸው  20 ዓመት  በታች  የሆኑ  የየአገራቱ  የእጅ  ኳስ  ብሔራዊ  ቡድን  ተጫዋች  የሚሳተፉ ይሆናል። 
                                                                                                                                                                         ምንጭ፦ ኢዜአ

No comments:

Post a Comment