የኢትዮጵያ ማሪታይም አካዳሚ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመካኒካል
እና ኤሌክትሪክ ኢንጅነሪግ የትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ በባሕር ምህንድስና አሰልጥኖ አስመርቋል።
የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር ጆርዳን በክር በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ
ላይ ተመራቂዎች ዓለም አቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ የመርከብ ምህንድስና ንድፈ ሀሳብና የተግባር ሥልጠናዎችን ለስድስት ወራት
ተከታትለዋል። የኢትዮጵያ
ማሪታይም አካዳሚ በዚህ ዙር 50 የኤሌክትሪካል መሀንድሶችንና 45 መካኒካል መሀንድሶችን በድምሩ 95 ባህርተኞችን ነው
ያስመረቀው። ተመራቂዎችም ለበርካታ አመታት
በዘርፉ ላይ የካበተ ልምድ ባላቸው መምህራን የወሰዱት እውቀት በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።
በባሕር
ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ማሪታይም አካዳሚ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ብዙ ግብራም ዘርፉ የስራ እድል ከመፍጠሩም ባለፈ
ለሃገሪቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ አስገኝቷል።
ተቋሙ
አሁን ያስመረቃቸው ባህርተኞች በመካኒካል ምህንድስና ለ8ኛ ጊዜ፣ እንዲሁም በኤሌክትሪካል ምህንድስና ዘርፍ ደግሞ ለ3ተኛ ጊዜ
ነው። በባሕር
ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ማሪታይም አካዳሚ እስከአሁን ድረስ ከ8 መቶ በላይ የባሕር ምህንድስና እጩ መኮንንኖችን አሰልጥኖ
አስመርቋል።
ምንጭ ፡- አ.ብ.መ.ድ
ምንጭ ፡- አ.ብ.መ.ድ
No comments:
Post a Comment