ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ በግብርናው ዘርፍ ላበረከቱት
አስተዋፅኦ የ2014ቱን የያራ ሽልማት ተቀበሉ፡፡ፕሮፌሰር ተካልኝ ሽልማቱን ሲቀበሉም "ሽልማቱ
ለእኔ ብቻ የተበረከተ ሳይሆን በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች፣ለመላው አርሶ አደርና ለኢትዮጵያ የተሰጠ እውቅና ነው" ብለዋል፡፡
የግብርና ሚንስትር ዴኤታ አቶ ወንድራድ ማንደፍሮ በስነ ስርአቱ ላይ እንዳሉት
ኢትዮጵያ የአፈር ለምነትን ለማረጋገጥ ባደረገችው ሰፊ ጥረት የፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ ድርሻ የመሪነቱን
ሚና ይወስዳል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር በአማካሪነትና በሚንስትር
ድኤታነት ሀገራቸውን እያገለገሉ ያሉት ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ ፣ በአፈር ምርምር፣ በምግብ ዋስትናና በአካባቢ ጥበቃ ባበረከቱት
የጎላ አስተዋፅኦ ነው ለያራ ሽልማት የበቁት፡፡
ፕሮፌሰሩ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው የአረንጓዴ አብዮት መድረክ ጎን ለጎን በተዘጋጀ መድረክ ላይ ነው ሽልማቱ የተበረከተላቸው፡፡ ሽልማቱም 60 ሺህ የአሜሪካን ዶላር አስገኝቶላቸዋል፡፡ በግብርና ላይ ስኬታማ ስራ ላበረከቱ ግለሰቦች ሽልማት የሚሰጠው ያራ፣ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ቀመር ከ2005 ወዲህ ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞን ጨምሮ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊና ዶክተር እሌኒ ገ/መድህንን ሲሸልም ለ3ኛ ጊዜ ነው፡፡
ምንጭ ፡- ኢብኮ/EBC/
No comments:
Post a Comment