የመጀመሪያዋ ወደ
ኢትዮጵያ
የመጣችው
አውሮፕላን
ፓቴዝ
ትባላለች::
የመጣችውም
ከፈረንሳይ
በ1922
ሲሆን
የዚህች
አውሮፕላን
ገጣጣሚ
አንድሬ
ሜሬዝ
የተባለ
ፈረንሳዊ
ነው::
የመጀመሪያዋ
ኢትዮጵያ
ውስጥ
የተገጣጠመችው
አውሮፕላን
ደግሞ "ፀሐይ" ስትባል
ይህን
ስያሜ
ያገኘችውም
በአጼ
ኃይለስላሴ
ሴት
ልጅ
በልዕልት
ፀሐይ
ኃ/ስላሴ
ስም
ነበር::
ነገር
ግን
ይህችን
አውሮፕላን
የገጣጠማት
ጀርመናዊ
አውሮፕላኗን
ኢትዮጵያ
አንድ
በማለት
ነበር
የሰየማት::
አውሮፕላኗ በ1928ዓ.ም ነው በጀርመናዊው ለዲግ ዌበር የመገጣጠም ስራዋ የተጠናቀቀው፡፡ በዚሁ ዓመት በታህሳስ ወር
የመጀመሪያ በረራዋን 150 ሜትር በማኮብኮብ ጀመረች፡፡
ሁለት መቀመጫ
ያላት ይቺ አውሮፕላን ወርዷ 7.32ሜ፣ 115 የፈረስ ጉልበት ሲኖራት በሰዓት 158ኪ.ሜ ትበራለች፡፡ ይህ ከፍተኛ ፍጥነቷ ሲሆን
ግሩም ድንቅ የማስተማሪያ አውሮፕላን ነበረች፡፡ ኢትጵያ አንድ/ፀሐይ/ አውሮፕላን ጣሊያኖች አዲስ አበባ ከመግባታቸው በፊት
ጠቅላላ የበረረችው 30 ሰዓት ብቻ ነበር፡፡ ጣሊያኖችም ጃንሜዳ ዛፍ ስር ቆማ ያገኟትና ለጥቂት ጊዜ አዲስ አበባ አካባቢ ካበረሯት
በኃላ ወደ አገራቸው ወስደው ቪኛ ዲቪሌ ሙዚየም ውስጥ አስቀመጧት፡፡ እስካሁን ድረስም “የንጉስ አውሮፕላን” በመባል ለህዝብ
ትታያለች፡፡
የብር መስሪያ መኪና አዲስ አበባ የገባው በሰኔ ወር 1895ዓ.ም ሲሆን
ስራውንም እንደገባ ጀመረ፡፡ የመጀመሪያውን የብር አሰራር ቅርፅ ዲዛይን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው ላ ግራኝ የተባለ ሰው
ነው፡፡ ከብር በታች ያሉትን ቅንስናሽ ገንዘቦች ቅርፅ ያወጣው ደግሞ ፈረንሳዊው ቻፕሊን ይባላል፡፡ለመጀመሪያ
ጊዜ
በፈረንሳይ ፓሪስ በምኒሊክ መልክ
ታትመው
የወጡት
ገንዘቦች
ስራ
ላይ
የዋሉት
ባንክ ከመቋቋሙ በፊት በ1886 ዓ.ም
ነበር::
የመጀመሪያው የሀገራችን ሆስፒታል ስራውን የጀመረው መጋቢት 7 ቀን በ1890
ዓ.ም ሲሆን ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ይባላል:: የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዶክተር /ዶክተር ማርቲን/ እየተባሉ የሚጠሩት ሃኪም ወርቅነህ እሸቴ ነበሩ::
ምንጭ:- ህብር ኢትዮጵያ
ምንጭ:- ህብር ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment