በዛሬው እለት ኢትዮጲያ በምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የሆነውን የህዋ ቴሌስኮፕ ያካተተውን የመጀመሪያው ዙር የህዋ ምርምር ፕሮግራሟን ይፋ አደረገች። ቅዳሜ ይፋ በሆነ መንገድ ስራውን የሚጀምረው የህዋ መመልከቻ (Observatory) ሁለት ስፋታቸው አንድ ሜትር
ርዝመት ያላቸው ቴሌስኮፓችን አካቶ ፕላኔቶችን ክዋክብትን ያለንበትንና ሌሎች በርቀት የሚገኙ የክዋክብት ስብስቦችን
ለማጥናት እንደሚረዳ ታውቋል።
እንጦጦ ላይ የሚገኘውን ይህን የህዋ መመልከቻ ጣቢያ በ 2.4ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለማስገንባት ሙሉ ወጪውን የሸፈኑት ሼህ መሀመድ አላሙዲ ናቸው። የህዋ መመልከቻውን ያስገነባው የኢትዮጲያ የህዋ ሳይንስ ማህበር (ESSS) ሌላ የህዋ መመልከቻ በታሪካዊዋ የላሊበላ ከተማ ዙሪያ ባሉ ተራሮች ላይም ለመገንባት በዝግጅት ላይ ነው። ኢትዮጲያ ለሜትሮሎጂና ለኮሚኒኬሽን ግልጋሎት የሚረዳ የመጀመሪያውን ሳተላይት በቀጣይ አመታት ውስጥ እንደምታመጥቅም ተጠቅሷል።
No comments:
Post a Comment