Wednesday, July 23, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተሸለሙ

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ስራ አስፈጸሚው አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ላበረከቱት አስተዋጽኦ የወርቅ ሜዳሊያ ሸለመ።

  የቦርዱ ሰብሳቢ  አቶ አዲሱ ለገሰ እንዳሉት ስራ አስፈጻሚውና ሰራተኞቹ አየር መንገዱ ውጤታማ እንዲሆንና ራዕዩ እንዲሳካ የላቀ ድርሻ አበርክተዋል። አየር መንገዱ ለአገሪቱ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት የላቀ ድርሻ ያለው በመሆኑ ቦርዱ ለአመራሮችና ሰራተኞች የቻለውን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል።
  ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ተወልደ ገብረማሪያም በበኩላቸው  ሽልማቱ የኔ ብቻ ሳይሆን አየር መንገዱ እንዲያድግ ያገዙ አመራርና ሰራተኞች ጭምር ነው ብለዋል። ቦርዱ ለስራችን እውቅና ስለሰጠን ተደስተናል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ሽልማቱ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ከማገዙም ባሻገር አየር መንገዱ የ2025 ግቡን ለማሳካት እንድንስራ ይረዳናል ብለዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው ዓመት ከዓለማችን ግዙፍና ምርጥ 50 አየር መንገዶች ጋር በመወዳደር በትርፋማነቱ 18ኛ ደረጃ መያዙ ይታወሳል።
                                            ምንጭ ፡- ኢዜአ 

No comments:

Post a Comment