Sunday, July 20, 2014

የአፄ ኃይለስላሴ የልጅነት ታሪክ……

ይህ የሀይለስላሴ የልጅነት ፎቶ ነው። አፈጣጠራቸው እጅግ አስገራሚና እድለኛ ናቸው ማለት ይቻላል። እድለኛ ያልኩት፦ ከንግስና ወንበር በመቀመጣቸውና ሀገሪቱን በመምራታቸው አይደለም። 
  እናታቸው ወይዘሮ የሺእመቤት 12 አመታቸው የሀይለስላሴን አባት ራስ_መኮንን ካገቡ በኃላ ለስምንት ጊዜ ያህል፤ አርግዘው እየጨነገፈባቸውና እየሞተባቸው ወልዶ መሳም ናፍቋቸው ቆዩና 9 ጊዜ ያረገዙት፦ልጅ ይቺን አለም በሰላም ተቀላቀለ። ልጁ ኢትዮጵያን 50 አመት በንግስና ይመራል ብሎ የጠበቀ ባይኖርም መፈጠሩ በራሱ ለእናቱ ለወይዘሮ የሺእመቤት ከንጉስም በላይ ነበር።
  ስምንት ልጅ ለፍሬ ሳይበቃ ለመከነባቸው እናት፦የሀይለስላሴ እስከ ሁለት አመት በህይወት መቆየት ፈጣሪ ተጨማሪ ልጅ ይሰጠኛል የሚለው እምነታቸው በውስጣቸው እንዲዳብር ምክንያት ሆኖዋቸው ነበር። እናም ለሀይለስላሴ፦ታናሽ እህት ወይም ወንድም ልፍጠር ብለው ከሁለት አመት በኃላ አርግዘው ቢገላገሉም ህፃኑ እንደተወለደ ሲሞት፤ የአፄ ኃይለስላሴ እናት / የሺእመቤትም በዚሁ ወሊድ ምክንያት ይቺን አለም በሞት ተሰናበቱ።በተደጋጋሚ ወሊድና ሀዘን መጎዳታቸው ሳያንስ ይቺን ምድር ብዙ ሳይጠግቡ በተወለዱ 30 አመታቸው፤ ከራስ መኮንን በተጋቡ 18ተ አመታቸው፤ ሀይለስላሴን በወለዱ 2 አመት 8 ወር መጋቢት 6 ,1884 ህይወታቸው አለፈ።አባትየው ራስ_መኮንን ወልደሚካሄልም እርሳቸው በሞቱ 14 አመታቸው በዚያው በመጋቢት ወር ድንገት ታመሙና ለህክምና ወደ አዲስ አበባ ሊያመጧቸው መንገድ ጀምረው ቁልቢ_ከተማ ላይ አረፉ።ሁለቱንም ወላጆች በልጅነት እድሜ ላጣ ብቸኛ ልጅ በህይወት ኖሮ "ታላቋን_ኢትዮጵያ" መምራት መቻል የፈጣሪ ስራ እንጂ የእሳቸው ብቃት ነው ትላላችሁ….. ?
  አፄ ኃይለስላሴም ኢትዮጵያን ለ50 አመታት ያህል በንግስና ከመሩ በኃላ እ.ኤ.አ ነሀሴ 27 /1975 ህይወታቸው አልፏል፡፡ የፊታችን ዕሮብ እ.ኤ.አ ሀምሌ 23 /1892 የተወለዱበት ዕለት በልጆቻቸው እና በአድናቂዎቻቸው ታስቦ ይውላል፡፡
                                       ምንጭ ፡- ኢቢኤስ /Ebs TV/

No comments:

Post a Comment