Saturday, July 5, 2014

ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተቀበሉ

      ሰኔ 28/2006 /  የቀድሞው የናይጀርያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል፡፡  

  የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ባፀደቅው መሰረት ኦባሳንጆ ለአፍሪካ ሰላምና ዴሞክራሲ መዳበር፣ በአህጉሩ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ፣ሙስናን ለመቀነስ በሚደረገው ርብርብ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረትና ኔፓድ ድርጅቶች ውስጥ ላሳዩት የላቀ ትጋት እያበረከቱት ላለው ከፍተኛ ስራ እውቅና በመስጠት በህግ የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል፡፡

  ኦሊሶጎን ኦባሳንጆ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አነሳሽነት ለተመሰረተው ጣና ከፍተኛ የደህንነት መድረክ ፕሬዝዳንትና መስራች ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment