Sunday, July 20, 2014

አዳማ አዲስ ማስተር ፕላን ሊሰራላት ነው


 በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ላለችው የአዳማ ከተማ በኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ ቴክኒካዊ ድጋፍና በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ አዲስ ማስተር ፕላን ሊዘጋጅላት መሆኑ ታውቋል፡፡በአዲሱ ማስተር ፕላን ከተማዋ የመኖሪያ፣ የንግድ እና የኢንዱስትሪ ዞንና ሌሎችም እንደሚኖሯት ተገልጿል፡፡


 ከአዲስ አበባ 98 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ውስጥ የምትገኘው አዳማ .. 1915 የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ዝርጋታን ተከትሎ እንደተቆረቆረች ይነገራል፡፡ 136.6 ስክዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈችው አዳማ 300,000 ህዝብ ይኖርባታል፡፡

                                          ምንጭ ፡ - ድሬ ቲዩብ

No comments:

Post a Comment