የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከማንኛውም ውድድር ማገዱን አስታወቀ። ፌዴሬሽኑ ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በጻፈው ደብዳቤ፥ ባለፈው ዓመት ክለቡን ካገለገሉት ስምንት ተጫዋቾች ጋር በተያያዘ ጥር 14 ቀን 2012 ዓ.ም በፍትህ አካላት በ10 ቀናት ውስጥ ውሳኔውን እንዲተገብሩ የጊዜ ገደብ ተሰጥቷቸው እንደነበር አስታውቋል።
ይሁን እንጅ ወልዋሎዎች በሚመለከተው የፍትህ አካል የተላለፈውን ውሳኔ በተሰጣቸው ጊዜ መሰረት አለመፈጸማቸውን ገልጿል። ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክለቡ ፌዴሬሽኑ ከሚሰጣቸው ማናቸውም አገልግሎቶች መታገዱን ነው ያስታወቀው።
ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment