Tuesday, March 17, 2015

የተ.መ.ድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በአዲስ አበባ…..

 

1928 ዓ.ም. የጣሊያን ፋሺስቶች አዲስ አበባን ወርረው ዋና ከተማቸው አደረጉዋት፤ እስከ 1931 ድረስ የኢጣልያ ምስራቅ አፍሪቃ አገረ ገዥ መቀመጫ ነበረች። የኢጣልያ ሠራዊት በኢትዮጵያውያን አርበኞች ተጋድሎና በእንግሊዝ ጭፍሮች ዕርዳታ ከተሸነፈ በኋላ፤ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከ5 ዓመት ስደት በኋላ ግንቦት 1933 ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። ወዲያው ከተማይቱ እንደገና የኢትዮጵያ ዋና ከተማ እንድትሆንም መሠረታዊ ሥራ ጀመሩ።

  በመሆኑም ግንቦት17 ቀን 1955 .. የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት (OAU) አስመሠረቱ፤ ይህም የሆነው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ እንዲቆይ በመጋበዛቸው ነው። ይህ ድርጅት 1994 ወደ አፍሪካ ኅብረት (AU) ተተካ፤ ዋና መሥሪያ ቤቱም እዚያው አዲስ አበባ ላይ እንዲቀጥል ተደርጓል። እንደዚሁም በተባበሩት መንግሥታት  የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና  መሥሪያ ቤት የሚገኘውም አዲስ አበባ ውስጥ ነው።
 አዲስ አበባ በተመድ ተቋማት እንቅስቃሴ ከኒውዮርክ እና ጄኔቫ በመቀጠል ሶስተኛዋ ከተማ ለመሆን በቅታለች
 

   ኢትዮጵያ 50 ዓመታት በፊት የመጀመሪያውንና የአፍሪካ አዳራሽ ተብሎ የተሰየመውን ሕንፃ ለአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አገልግሎት እንዲውል በስጦታ አበርክታለች፡፡ 1951.. የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሲመሠረት፣ የአፍሪካ ሕዝቦች ከወቅቱ የቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የሚታገሉበት ጊዜ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በውጭ የሚኖሩ የአፍሪካ ልጆችም ለአህጉሪቱ ነፃ መውጣት፣ ለሕዝቦች እኩልነትና ክብር ሲታገሉ በነበረበት ወቅት ነበር የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዕውን የሆነው፡፡ 

   አዲስ የተገነባው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ህንፃ አዲስ አበባን ከኒዮርክ እና ከጄኔቫ በመቀጠል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በርካታ ፅህፈት ቤቶች የሚገኝባት ከተማ ያደርጋታል፡፡ ህንፃው በድርጅቱ ስር ያሉ እንደ ዩኒሴፍ ፣ የተመድ የስደተኞች መርጃ ድርጅት እና የአለም ጤና ድርጅትን የመሳሰሉትን በርካታ ተቋማት በአንድ ቦታ ለማሰባሰብ ያስችላል፡፡ ለሕንፃው ግንባታ አሥር ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ 1800 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እዚያው በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቅጥረ ግቢ ውስጥ የተገነባ ነው፡፡ 

    የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 5 ግዙፍ አህጉራዊ ድርጅቶች አንዱ ነው፡፡ ይህ ተቋም ከብኄራ ቤጸ መንግሽጽ ፊት ለፊት የሚገኘው ይህ ህንፃ በእምነበረድ የተንቆጠቆጠ ከመሆኑም በላይ የዕውቁ ሰዓሊ እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፍወርቅ ተክሌ የሞዛይክ ስራዎች ውበት እና ድምቀት ሰጥተውታል፡፡ ህንፃው ለተለያዩ አለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ስብሰባዎች የሚያገለግሉ ዘመናዊ የስብሰባ አዳራሾች ናቸው፡

No comments:

Post a Comment