Thursday, January 29, 2015

የሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ 94ኛ ዓመት የልደት በዓል ትላንት ተከበረ


  በጣሊያን ዳግም ወረራ ወቅት 15 አመታቸው ከፋሽስት ወራሪ ጦር ጋር በተለያዩ አውደ ግንባሮች ተፋልመው ከፍተኛ ጀብዱ የፈፀሙት እና ጣሊያን ከአገር ተሸንፎ ከወጣ በኋላም የአገር ዳር ድንበርን በማስጠበቅ ከፍተኛ ጀግንነት የፈፀሙት የሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ 94 የልደት በዓል ትላንት ጥር 20 ቀን 2007 .. ተከብሯል፡፡


  በ1929 . ጣሊያን  40 ዓመታት የአድዋ ሽንፈት በኋላ  ዳግም ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ገና 15 ዓመት ወጣትነት ዕድሜያቸው የራሳቸውን ጦር በማደራጀት ጠላትን የተዋጉት /ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በወቅቱ በተለያዩ የጦር ውሎዎች በጠላት ላይ ከፍተኛ ጀብዱን ተቀዳጅተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ሶማሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት የአገርን ዳር ድንበር በማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡


  ሌ/ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ጥር 20 ቀን 1913 .. የተወለዱ ሲሆን፤ በትላንትናው ዕለት ቀበና አካባቢ በሚገኘው የልጃቸው የትምወርቅ ጃጋማ ቤት የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት 94 አመት የልደት በዓላቸውን አክብረዋል፡፡ /ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን ከነበሩት ጀኔራሎች መካከል በአሁን ወቅት በህይወት ከሚገኙት ሁለት ጀኔራሎች (በውጭ ሀገር የሚገኙት /ጀኔራል ወልደስላሴ በረካ እና ሀገር ውስጥ ያሉት 94 ዓመቱ /ጀኔራል ጃገማ ኬሎ) አንዱ ሲሆኑ፤ጀኔራሉ አንድ ወንድና አምስት ሴት ልጆች፣ አምስት የልጅ ልጆችና አራት የልጅ ልጅ ልጆችን አፍርተዋል፡፡


 /ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በህይወት እያሉ በደራሲ ፍቅረ-ማርቆስ ደስታጃገማ ኬሎ የበጋው መብረቅ” በሚል የህይወት ታሪካቸው ተፅፏል፡፡ ሌ/ጀነራል ጃገማ 15 አመት ዕድሜያቸው ወራሪውን የጣሊያንን ጦር ለመዋጋት ከዘመቱበት የአርበኝነት ገድል ጀምሮ እስከ መደበኛው የሀገሪቱ መካላከያ ጦር ድረስ ለኢትዮጵያ እና ለህዝቧ ነፃነት እና ክብር ሲሉ በርካታ የጦር ገድሎችን መፈፀማቸው ይታወቃል፡፡

No comments:

Post a Comment