Wednesday, January 21, 2015

የሚሊዮኖች ተስፋ…….. የአለም ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ


 1987 - 2009(..) ካሉት የአለም የምግብ ተሸላሚዎች ውስጥ ከፍተኛውን ደረጃ ይዘው የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ እና የህንድ ተመራማሪዎች ናቸው፡፡ 2009 ደግሞ ኢትዮጵያ በፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ የአለምየምግብ ሽልማትን አግኝታለች፡፡ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ ድርቅን እና አቀንጭራን የሚከላከለውን የማሽላ ዝርያ አግኝተዋል፡፡  2009 የአለም የምግብ ሽልማት ድርጅት /FAO/ ተሸላሚ ሲሆኑ በምርምር
 ውጤታቸውም በአለም ላይ ከግማሽ ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ ህዝቦችን ተጠቃሚ አድርገዋል፡፡


 ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ ለተቋቋመው የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ አባልነትም ተመርጠዋል፡፡ ፕሮፌሰር ገቢሳ 26 አባላትን ላካተተው የተባበሩት መንግስታት የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ ሲመረጥ ብቸኛው የእርሻ ሳይንቲስት እንደሆኑ የተለያዩ አለም አቀፍ የብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡ ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ በአለም አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል፡፡ ከአለም የምግብ ሽልማት ድርጅት የተሰጣቸውን 250,000 ዶላር እና ሌላ ገንዘብ በማሰባሰብ ፋውንዴሽን ለማቋቋም አስበዋል፡፡

  
   የአለም ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ የምርምር ውጤት የሆነው የማሽላ ዝርያ ከሰሃራ በታች ለሚገኙ አገራት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያስቻለ ይገኛል፡፡ ይሄው የማሽላ ዝርያ ምርቱ ከፍተኛ ፣ በንጥረ ነገር የበለፀገ እንዲሁም ድርቅ ፣ ውርጭ ፣ ተባይ ፣ በሽታ እና አቀንጭራን የመቋቋም አቅም አለው፡፡ 


  ሎሬቱ በፐርዱ ዩኒቨርስቲ የእፀዋት ማራባት ፕሮግራም ድርቅን እና አቀንጭራን የሚቋቋሙ ብዙ የማሽላ ዝርያዎችን አጥንተዋል፡፡ ይህም በፊት አርሶ አደሩ ይጠቀም ከነበረው ዝርያ በ10 እጥፍ ምርታማነትን ያሳድጋል፡፡ ድርቅ እና አቀንጭራን በመቋቋም ከፍተኛ ምርት ይሰጣሉ የተባሉት የማሽላ ዝርያዎችም ለሀገራችን አርሶ አደሮች ተሰራጭተው ውጤታማ ሆነዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የፕሮፌሰሩ አስተዋፅኦ የላቀ ነው፡፡


  ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ 1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አለም ፣ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጅማ እርሻ ኮሌጅ አዳሪ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡ ከዚያም ትምህርታቸውን አጠናክረው በመቀጠልም “በፅዋት ሳይንስ” ከሀሮማያ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡ በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ እየተማሩ እያለም የውጭ እድል አግኝተው በፐርዱ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዲግሪያቸውን /ፒኤች ዲግሪያቸውን/ አግኝተዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ ….. https://www.youtube.com/watch?v=QMMTMDq_SSg

No comments:

Post a Comment