Wednesday, February 4, 2015

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት እና ተመራማሪነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሶስት መምህራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡

 

   የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶከተር ዮሴፍ ማሞ እንዳስታወቁት የፕሮፌሰርነት ማዕረጉ ለመምህራኑ የተሰጠው የዩኒቨርስቲው ሴኔት በወሰነው መሰረት ነው፡፡ በዚህም ለዩኒቨርስቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ይፍሩ ብርሃን ለእንሰሳት ህክምና ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ኢታና ደበላ እና ለስነ ህይወት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ፍቅሬ ደሳለኝ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል፡፡


መምህራኑ ከረዳት ፕሮፌሰር እስከ ተባባሪ ፕሮፌሰር በቆዩባቸው ጊዜ ያከናወኗቸው የምርምር ስራዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ባላቸው የምርምር ስራ በሚያትሙ የህትመት ውጤቶች ታትመው የወጡት በዩኒቨርስቲው ተገምግሞ ለፕሮፌሰርነት ብቁ የሚያደርጋቸው መሆኑ ታምኖበታል ብለዋል፡፡ እንደ ኢ.ዜ.አ የምርምር ስራዎች ለአካባቢው ማህበረሰብ እና ለአገር ጥቅም እንዲሰጡ ለማድረግ ዩኒቨርስቲው የምርምር ጥናት ኢንስቲትዩት አቋቁሞ  ወደ ስራ መግባቱን አመልክቷል፡፡

No comments:

Post a Comment