Monday, January 12, 2015

ፒያሳ አካባቢ የሚገኘው የጣይቱ ሆቴል በድንገተኛ የእሳት አደጋ ተቃጠለ፡፡


  በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዘመናዊ ሆቴል የሆነውና ለሀገሪቱ እና ለሕዝቡ እንደ ታላቅ ቅርስ የሚታየው ጣይቱ ሆቴል ተቃጠለ። የቀድሞው እቴጌ የአሁኑ ጣይቱ ሆቴል 1898. በነሀሴ ወር ስራውን እንደጀመረ ይነገራል፡፡ 109 ዓመታትን አስቆጥሯል ማለት ነው፡፡ 1900. ጥቅምት 25 ቀን አፄ ምኒልክ በአዲስ አበባ ያሉ ዲፕሎማቶችን እና የውጭ አገር ሰዎችን ጋብዘው ሆቴሉን አስመረቁ፡፡ የመጀመሪያው የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ ሙሴ ፍሬድሪክ ሀል ነበር፡፡ ይህ ሆቴል ነው እንግዲህ ጥር 3/ 2007. በእሳት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የወደመው፡፡


  ጣይቱ እጅ የሚያስቆረጥም ወጥ እያሠሩ ገበያ ቢጠብቁ ጠፋ:: እንኳን ምግብ መብላት ከግሪኮቹ ሻይ ቤት ገብቶ ሻይ መጠጣት ነውር ነበረና: ጣይቱ ጠዋት የሚያሠሩት ወጥ ለሠራተኞቹ የማታ ራት ይሆን ጀመር:: የሚስታቸው ገበያ ማጣት ያሳሰባቸው አጤ ምኒልክ አንድ ቀን ከችሎት ሊነሱ ሲሉ በአካባቢያቸው ላሉ መኩዋንንቶች "ጣይቱ ምግብ የሚሸጥበት ቤት ከፍታለችና እንሂድና ልጋብዛችሁ" ብለው ወሰዱዋቸው:: .መኳንቶቹ በሉ ጠጡና ምኒልክ 30ብር ከፈሉ::
 


   በማግሥቱ እንደተለመደው ገበያ ቢጠበቅ ጠፋ:: ቀጥሎም ጠፋ; ቀጥሎም ጠፋ:: እንደገና ምኒልክ ሆቴል ገብቶ መብላት ነውር ያለ መሆኑን ለመኳንንቱ ገልፀው እንደገና ምሣ ጋበዙ:: በሌላው ቀን አሁንም ገበያ አልተገኘም:: ቢጠበቅ ቢጠበቅ ድርሽ የሚል ሰው ጠፋ::

  በሌላ ቀን ደግሞ አጤ ምኒልክ ከችሎት ሊነሱ ሲሉ በዙሪያቸው ላሉ መኳንንት "ሰማችሁ ወዳጆቼ" አሉ:: "በፈረንጅ አገር አንድ ቀን አንድ ሰው የጋበዘ እንደሆነ የተጋበዘ ሰው በሌላ ቀን ደግሞ ብድሩን ይከፍላል ብድሩን ካልከፈለ ግን እንደ ነውር ይቆጠርበታል:: "ብለው ንግግራቸውን ሳይጨርሱ መኳንንቱ "እርስዎን ፈርተንና አፍረን ነው እንጂ የሚሆንልን ከሆነ የምኒልክን ብድር ለመመለስ እኔ አለሁ" እያሉ ተራ በተራ ከሆቴል ቤት ምኒልክንና ጣይቱን ይጋብዙ ጀመረ::  ገበያ እየደራ ሄደ:: “ምሳችንን እቴጌ ሆቴል ሄደን እንብላየሚለው ስለበዛም ስሙ እቴጌ ሆቴል ተባለ::
        
                                 (ጳውሎስ ኞኞ፣ አጤ ምኒልክ)

No comments:

Post a Comment