Saturday, January 10, 2015

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ በ106 ዓመታቸው ዐረፉ


  ብፁዕ አቡነ አረጋዊ 1901 .. በፀለምት /ሰሜን ጎንደር/ ተወልደው ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ ትምህርት ቤት ገብተው ንባብና ዳዊት እንዲሁም ፀዋትወ ዜማ አጠናቅቀው ከብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ማዕርገ ዲቁናና ማዕርገ ቅስና ተቀብለዋል፡፡ በዋልድባ አብረንታንት ገዳም ገብተው ለዘጠኝ ዓመታት ያህል (1933 - 1942 ..) ሥርዓተ ገዳሙን ከአጠኑና በግብዝና ከአገለገሉ በኋላ በዚሁ ገዳም መዓርገ ምንኵስናን ተቀብለዋል፡፡ ትምህርታቸውን በመቀጠል በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በሚገኘው በደብረ ዓባይ ገዳም የደብረ ዓባይ መዝገበ ቅዳሴ ዜማ ተምረው በመምህርነት ተመርቀዋል
፡፡

  በ1943 .. በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ፈቃድና ትእዛዝ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትን እንዲያገለግሉ ተልከው ለአራት ዓመታት ያህል አገልግለዋል፡፡ አሁንም በቅዱስ ፓትርያርኩ ፈቃድ ወደ ግብጽ ሔደው 16 ዓመታት ያህል ነገረ መለኰትን በዓረብኛ ቋንቋ አጥንተው ተመርቀዋል፡፡ 

  ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ በሱዳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በኃላፊነት ለማገልገል ተልከው ለስድስት ዓመታት ያህል በአስተዳዳሪነት ሠርተዋል፡፡ በዚሁ ላፊነት ሳሉም 1968  .. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ሆነው በተሾሙ ጊዜ በሱዳን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ወክለው በመምጣት ለበዓሉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል
፡፡

  1972 .. በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በቅዱስ ፓትርያርኩ ፈቃድ የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቀ ሥልጣናት በመሆን አገልግለዋል፡፡ በበፊት ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት ገብረ ማርያም ገብረ ሥላሴ ይባሉ የነበሩት ብፁዕነታቸው፣ አቡነ አረጋዊ ተብለው በጥቅምት ወር 1983 .. በሱዳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሆነው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አንብሮተ እድ ተሾመዋል
፡፡

  
  ከመጋቢት 1985 .. ጀምሮ የኢሉባቦርና የጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳ ሆነው ለአንድ ዓመት ያህል ሠርተዋል፡፡ ከየካቲት 1986 .. ጀምሮ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳምና /ቤት የበላይ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከሐምሌ 1968 .. ጀምሮ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከግንቦት 1992 .. ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ተዛውረው የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ በመጨረሻም በዚሁ ሥራ ላይ ሳሉ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 1 ቀን 2007 .. በተወለዱ 106 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል፡፡


   የቀብራቸው ሥነ ሥርዓትም በዚሁ ዕለት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባሉበትና የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት ሥርዓተ ጸሎተ ፍትሐቱ ከተፈጸመ በኋላ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

No comments:

Post a Comment