Tuesday, October 7, 2014

ኢትዮጵያ በሲሚንቶ ምርት ቀዳሚ ሆነች

  
  በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ በዓመት 12 ነጥብ 6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ በማምረት የቀዳሚነት ቦታውን ከኬንያ ተረክባለች፡፡ ኬንያ በቀጠናው በጎርጎሮሳውያኑ 2012 - 2013 ድረስ 7 ነጥብ 4 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ በዓመት በማምረት ቀዳሚ ነበረች፡፡ ኢትዮጵያ በዘርፉ መሪነቱን በመረከቧ ኬንያ አሁን ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ብላለች፡፡
  በአፍሪካ ከሰሃራ በታች 25 በመቶ የሚሆነውን ሲሚንቶ የምታመርተው ናይጄሪያ ስትሆን 16 በመቶውን ደቡብ አፍሪካ በማምረት በአፍሪካ ያለውን ገበያ ይይዛሉ፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ ከአፍሪካ 11 በመቶውን ሲምንቶ በማምረት በሶስተኝነት ስትከተል ኬንያ 6 በመቶ የሲሚንቶ ምርት በማምረት አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
  በዓለም ላይ በአማካይ የሲሚንቶ አጠቃቀም 5 መቶ ኪ.ግ በአመት ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ ግን ኬንያ 80 እና ኢትዮጵያ 61 ኪ.ግ አማካይ ላይ ደርሷል፡፡ ይህም በምስራቅ አፍሪካ እያደገ ያለው አማካይ የሲሚንቶ የአጠቃቀም መጠን ከፍተኛ የሲሚንቶ ምርት እንዲኖር የሚያደርግ አንደኛው መንገድ ነው ተብሏል፡፡
  በአፍሪካ እያደገ የመጣው የሲሚንቶ ምርት አህጉሪቷ ባለፉት አስር አመታት ከውጭ የምታስገባውን ሲሚንቱ በፍጥነት እንዲቀንስ አስችሎታል፡፡ በዚህ ረገድ ቀዳሚዋ ናይጄሪያ በጎርጎሮሳውያ 2010  አምስት መቶ ሚሊየን ዶላር በማውጣት ሲሚንቶን ከውጭ ስታስገባ በ2012 ግን ይህ ገንዘብ 139 ሚሊየን ዶላር ዝቅ ማለት ችሏል፡፡
  ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ የሲሚንቶ ምርት የመጠቀም አቅሟ እየጨመረ በመሆኑ ከውጭ ሲሚንቶ የማስገባት መጠኗ በ75 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡
                                                                                     ምንጭ፡- ካምፓኒስ ኤንድ ማርኬትስ ዶት

No comments:

Post a Comment