Thursday, December 31, 2020

ያልተዘመረለት ሁለገብ ባለሙያ ንጉሱ ጌታቸው ... !!!

 

ፀሀፊ ተውኔት ተዋናይ ዳይሬክተር እና አዘጋጅ እንዲሁም መምህር ነው፡፡ በገበና .1 ላይ የቅባቱን ገፀ ባህሪ ወክሎ ተጭውቷል(ደላላ ሆኖ ማለት ነው)፡፡ ሙዚቃዊ ተውኔትን በማዘጋጀትም ይታወቃል፡፡ በርከት ያሉ የመድረክ ተውኔቶች ልዩ ልዩ ፊልሞች እና የቴሌቭዥን ድራማዋች ላይ ሰርቷል አርቲስት ንጉሱ ጌታቸው።

እምቅ ምኞት ጥምዝ የተቋጠረ ደም ክፍተት የሺ እምባ ክታብ ግርዘት የነፃነት ድምፅ ግርዶች የቡሎ ጫካ ንጉስ እና ስደት የመሳሰሉ ታሪካዊ ትውፊታዊ እና ሙዚቃዊ ተውኔቶችን ደርሷል አዘጋጅቷልም፡፡

በፊልሞችም:- የጀግና ምድር ኤስ - 26 ሰንሰለት የታፈነ ፍቅር ግማሽ ሰው ይሉኝታ በመንገዴ ላይ ህያብ የፀሀይ መውጫ ልጆች ለጉድ የፈጠረሽ አነቃሽኝ ሴት አርበኛ እና ዮናታን የመሳስሉት ላይ በድርሰት በትወና እና ዳይሬክቲንግ ተሳትፏል፡፡


ገመና ቁጥር 1 (ቅባቱ - ደላላ) ለወደዱት ምዕርፍ 1 ላይ የኢንጅርነት ገፀ ባህሪን ወክሎ ተጫውቷል:: ለወደዱት ምዕራፍ 3 እና ችሎት እንዲሁም የአድዋ ትግል የተሰኙ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማዎችንም ድርሷል፡፡

በመምህርነት ደግሞ ወክማ ክርኤቲቭ እና . ዩኒቭርስቲ ያገለገለ ሲሆን እነ ዳይሬክተር ሄኖክ አየለ ተዋናይ ሚሊዮን ብርሃኔ ተዋናይት ሳሚያ እና ሌሎች ታዋቂ / ተወዳጅ/ የኪነ ጥበብ ሰዎችን አፍርቷል፡፡

 


ወደ ሙዚቃዊ ተውኔት የሚያደላው አርቲስት ንጉሱ ጌታቸው ታሪክ አዋቂ እና ተጨዋች ነው፡፡ የእነ ሌሬት ፀጋዬ / መድህን እና ተስፋዬ ገብሬ አድናቂ ሲሆን በስነ ፅሁፍ ስራው ላይ የእነሱ ተፅዕኖ እንዳደረበትም ይናገራል፡፡ በቀጣይ ለእይታ የሚቀርቡ በርካታ የመድረክ ተውኔቶች እጁ ላይ እንዳለም ጠቆም አድርጎኛል፡፡

በአጠቃላይ በሬዲዮ እንግዳ ዝግጅታችን ከሁለገቡ ባለሙያ ንጉሱ ጌታቸው ጋር ጥሩ ቆይታ ነበረን፡፡ የአሜን እና የያፌት አባት ለነበረን ጊዜ እጅ ነስቻለሁ፡፡ እድሜን ከጤና : ስራን ከስኬት ጋር ተመኝቻለሁ... ፡፡

No comments:

Post a Comment