የመድረክ ፈርጥ፣ የተውኔት ፀሃፊ እና አዘጋጅ እንዲሁም ምሁር ናቸው፡፡ በሃገር ፍቅር እና በብሄራዊ ትያትር ቤት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩንቭርስቲ ባህል ማዕከል /ቤተ ኪነ ጥበባት ወ ትያትር/ በሰራተኝነት እና በኃላፊነት ስርተዋል፡፡ ለረጅም አመታትም በመምህርነት ሙያ አገልግለዋል፡፡ በጥበቡ አለም ከ60 አመታት በላይ ያገለገሉ ሲሆን በእነዚህ አመታትም ከ100 በላይ የጥበብ ስራዎችን ለህዝብ አቅርበዋል፡፡ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ፡፡
- እዮብ - ሀምሌት - ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት
- የእሾህ አክሊል
- ኡመር ኻያ - ፍርዱን ለእናንተ
- የገና ገበያ - የሺ - ቴዎድሮስ
- አሉላ
አባነጋ - አጎቴ ቫኒያ - ሮሚዮና ዡሌት
- ባለካባ እና ባለዳባ
- ጠልፎ በኪሴ - ላቀችና ማሰሮ - አባት እና ልጆቹ እና ተሀድሶ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ጋሽ ተስፋዬ ከተውኔት ፀሀፊነት: አዘጋጅነት እና ተዋናይነት ባሻገር በጋዜጠኝነት ሙያም በኢትዮጵያ ሬዲዮ "በኪነ ጥበባት ጉዞ" እና በኢትዮጵያ ቴሌቭዝን "ህብረት ትርኢት" የተሰኙ ፕሮግራሞች ላይ ሰርተዋል፡፡
ከ10 በላይ መፅሃፍትን ለአንባቢ አድርሰዋል፤ እነሱም ፡-
1. ዕቃው (ተውኔት) 1961ዓ.ም
2. መተከዣ (ግጥም እና አጭር ልቦለድ) 1967ዓ.ም
3. መልክአ ዑመር (አዛማጅ ትርጉም) በ1986ዓ.ም
4. የወጣቱ ቨርተር ሰቀቀኖች (ትርጉም) 1997 ዓ.ም
5. የዑመር ኻያም ታሪካዊ ልቦለድ (አዛማጅ ትርጉም) 1999ዓ.ም
6. ጥንወት (ልቦለድ) 2000ዓ.ም
7. ጎህ ሲቀድ (የግጥም መድብል) 2001ዓ.ም
8. ሽልማቱ (ልቦለድ) 2002ዓ.ም
9. ይሉኝታ እና ፍቅር (ልቦለድ) 2002ዓ.ም
10. ረጅም ጉዞ ወደ ነፃነት (ትርጉም) 2009ዓ.ም
11. የመጨረሽታ መጀመርታ (ልቦለድ) 2010ዓ.ም
12. አሰብ እና ክበር (አዛማጅ ትርጉም) 2011ዓ.ም
13. መደበሪያ (ልቦለድ) 2013 ዓ.ም - ይህ መፅሃፍ የ84ኛ አመታቸውን ባከበሩበት ወቅት ለአንባቢያን ያበቁት ነው፡፡ ከእሳቸው ጋር ጥቂት ደቂቃዎችን ማሳለፍ መፅሃፍ ገልጦ እንደማንበብ ይቆጠራል፡፡ እኔም ይህን እድል በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በነበረችን ጥቂት ደቂቃዎች ብዙ እውቀት አግኝቻለሁ፡፡ ግለ ታሪካቸው በሌላ ሰው እየተፃፈ እንደሆነ ሹክ ብላኛል፡፡ እሱ ለንባብ ሲበቃ ስለ እሳቸው ብዙ ነገር እናገኛለን ብዬም አስባለሁ፡፡ ከእሳቸው ስራዎች እና የህይወት ልምድ እኔ በጥቂቱ አጋራኋችሁ፤ ቀሪውን እናንተ ጨምሩበት….