አጤ ምኒልክ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሆነው ዘውድ ከመጫናቸው በፊት በአንዳንድ አጋጣሚ ምክንያት
ከኢትዮጵያ ውጪ ወጥተው ዘመናዊ ትምህርት ለመቅሰም የቻሉ ቁጥራቸው በትክክል ይህን ያህል ተብሎ ባይታወቅም ከሄዱት መካከል ግን
ትምህርታቸውን ፈፅመው የተመለሱ እና ለወገናቸው ጥቅም ያበረከቱ ሶስት ኢትዮጵያውያን ይታወቃሉ፡፡ እነርሱም ከንቲባ ገብሩ ደስታ
፣ ሀኪም ወርቅነህ እሸቴ(ዶ/ር ማርቲን) እና አናሲሞስ ነሲቡ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ጥቂት ስለ ከንቲባ ገብሩ ደስታ መረጃ እንጋራ………
ከንቲባ ገብሩ ደስታ (1845 - 1949) እውነተኛ ስማቸው ጎባው ደሰታ ሲሆን የአቶ ደስታ ወልደእሰይ እና ወ/ሮ
ትርንጎ ተክሌ ልጅ ናቸው፡፡ የተወለዱትም ጎንደር ውስጥ አለፋጣቁሳ የሚባል አካባቢ ነው፡፡ ከንቲባ ገብሩ ከውጪ ትምህርት ቀስመው
ሲመለሱ ባሳዩት ችሎታ በራስ መኮንን የሐረር ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሸሙ፡፡ ቀጥሎም ከአድዋ ጦርነት በኋላ በአጤ ምኒልክ የመጀመሪያው
የጎንደር ከንቲባ ሆነዋል፡፡ በ1930 የመጀመሪያ ፓርላማ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆኑ፡፡ ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያ
ፓርላማ ፕሬዚዳንት ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከንቲባ ገብሩ አማርኛ ፣ ኦሮምኛ ፣ ጀርመንኛ ፣ ፈረንሳይኛ እና እንግሊዘኛ ይናገሩ ነበር፡፡
ከንቲባ ገብሩ የእማሆይ ፅጌ ማሪያም (የውብ ዳር) እና የክብርት
ዶ/ር ስንዱ ገብሩ አባት ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment