Tuesday, November 18, 2014

በሳምንቱ መጨረሻ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ድል ቀንቷቸዋል



 ስፔን፡- 2014/2015 የአገር አቋራጭ ውድድር መክፈቻ በቀዝቃዛ እና በነፋሻ ማለዳ ኢማና መርጊያ 4ተኛ ተከታታይ ድሉን ሲያስመዘግብ በላይነሽ ኦልጅራ በሴቶች አሸናፊ ሆናለች፡፡ በ2014/2015 የዓለም አገር አቋራጭ በስፔን ቡርጎስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በውድድሩ ሦስት ተከታታይ ወርቅ ማስመዝገብ የቻለው ኢማነ መርጊያ አሸንፏል፡፡


  ኢማነ መርጊያ ከሌላኛው ኢትዮጵያዊ ኢድሪስ ሙክታር ጋር ያደረገው ከፍተኛ የማሸነፍ ትግል የብዙዎችን ቀልብ መሳብ የቻለ ሲሆን ይማነ 9.8 ኪሎ ሜትሩን ለማጠናቀቅ 27 ደቂቃ 39 ሰከንድ ወስዶበታል፡፡ በውድድሩ በላይነሽ ኦልጅራም በሴቶቹ ባለድል መሆን ችላለች፡፡



 ኔዘርላንድ፡- በኔዘርላንድ በተደረገ 15 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አንደኛ እስከ አራተኛ ወጡ፣ አበራ ኩማ 4218 ቀዳሚ ሲሆን ይገረም ደመላሽ 4226 ሁለተኛ የኔው አላምረው 4230 ሶስተኛ ወጥቶአል፡፡

ቱርክ፡- በኢስታንቡል 36ተኛው ኢስታንቡል ማራቶን አማን ጎበና 22846 አሸናፊ ሆናለች፣ ሶሎሜ ጌትነት ሁለተኛ ወጥታለች፡፡ በወንዶቹ ሞሮኮዋዊውን ሀሊድ ቻኒ ተከትሎ ኢትዮጵያዊው ገቦ ቡርቃ 21223 ሁለተኛ ወጥቶአል፣ ዘንድሮ ያደረጋቸውን ሶስቱንም ውድድሮች ማሸነፍ የቻለው ገቦ የመጀመሪያ ሽንፈቱ ሆኖአል፡፡
 
ፈረንሳይ፡- 18ተኛው ቦሎኝ ግማሽ ማራቶን ይታያል አጥናፉ ኣሸናፊ ሲሆን ይሁንልኝ አዳነ ሶስተኛ ወጥቶአል፣ በሴቶች በቀለች በጻጻ ቀዳሚ ሆናለች፡፡

ስዊዝ፡- ኢትዮጵያዊው ኢፋ ባላድ 8ኪሎ ሜትር የጎዳና ውድድር አሸናፊ ሲሆን በሴቶች 6 ኪሎ ሜትር ለካናዳ የምትሮጠው አስቴር ደምሴ ሁለተኛ ወጥታለች፡፡

ጃፓን፡- ዮኮሀማ የሴቶች ማራቶን ቶኦሚ ታናካ ቀዳሚ ስትሆን ኢትዮጵያዊቷ ቲኪ ገላና 22913 ስድስተኛ ወጥታለች፡፡

No comments:

Post a Comment