ድምፃዊ እና የዜማ ደራሲ ነው፡፡ ወደ ሙዚቃው ከገባባት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ርዕሰ - ጉዳዮች ዙሪያ በርከት ያሉ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ሁለት ያህል አልበሞችም አሉት በግሉ ማለት ነው፡፡ ከግርማ ይፍራሸዋ ጋር የሰሩትም “መለያ ቀለሜ” የተሰኘ አልበም አለው፡፡ ሙዚቃን የጀመረው በእንግሊዘኛ ዘፈኖች ነው፡፡ “ሳይሽ እሳሳለሁ” ፣ “ውበትን ፍለጋ” ፣ ከዘሪቱ ከበደ ጋር የተጫወተው “ታምሪያለሽ” እና “ትዝታ” ከሰራቸው ነጠላ ዜማዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ አርቲስት ሚካኤል በላይነህ፡፡
በኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪክሲቲ
ከተመረቀ በኋላም በከተማ ፕላን ለአራት አመት ያህል አገልግሏል፡፡ በወቅቱ ይከፈለው የነበረው 420 ብር ስላላረካው ወደ ሌሎች
ሙያዎች እና ሙዚቃ ተሸጋገረ፡፡ ከዚያም ቦሌ መንገድ “ፐርፕል” የሚባል ካፌ ከሌሎች ሰዎች ጋር ከፍቶ ይሰራም ነበር፡፡ ካፌው ተወዳጅ
በመሆኑ በርካታ ሰዎች ይስተናገዱበት ነበር አርቲስቶችን ጨምሮ፡፡ ለአብነትም ላፎንቴኖች ፣ ጆኒ ራጋ ፣ ኤልያስ መልካ እና ቴዎድሮስ
ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ይጠቀሳሉ፡፡
አርቲስት ሚካኤል
በላይነህ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን በማንሳት በዛ ያሉ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ለአፍሪካ ህብረት በተሰራ ዘፈን ላይ በድምፅ ተሳትፏል፡፡
በተለይ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ላይ በርከት ያሉ
ዜማዎችን ደርሷል፡፡ በድምፅም ተሳትፏል፡፡ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፡- “ማለባበስ ይቅር - ማወቅ ነው መሰልጠን” ፣ “መላ
መላ” ፣ “መታመን ማመን ነው ” ፣ “ኦሮሚኛ - መሌ ሀራ” እና ሌሎች አራት ያህል ዜማዎችን ሰርቷል፡፡
በቅርቡም
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ /አባይ/ “ከፍ እንበል” የተሰኘውን ዘፈን ዜማ ደርሷል፡፡ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘም ከዘሪቱ
ከበደ ጋር በመሆን “ኢትዮጵያ አረንጓዴ” የሚል ስራም ሰርቷል፡፡ በተጨማሪም ለስኳር ህሙማን የተሰራ “ስኳርን አየሁት” የሚል ዜማም
አለው፡፡ ይህንን ዘፈን አብነት አጎናፍር ፣ ግርማ ተፈራ ፣ ሀይልዬ ታደሰ እና ጥላሁን ገሰሰ ተጫውተውታል፡፡
No comments:
Post a Comment