Thursday, April 3, 2014

ጥቂት ስለ አልዩ አምባ ….

 የአንኮበር ታሪክ ሲዘከር የስምጥ ሸለቆ አካል የሆነችው የአልዩ አምባ ከተማና የአብዱል ረሱል የእስልምና መቃብር ሥፍራ አብረው የሚጠቀሱ ናቸው። አልዩ አምባ ከአንኮበር ከተማ አሥራ ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ቁልቁል ሲወረድ ትገኛለች። እንደ ሐረር በግንብ የተከበበች ስትሆን በምስራቅ፣ በደቡብና በምዕራብ በሮች አሏት። ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ ከሚባሉት የቀረጥ ኬላዎችና የንግድ ማዕከል አንደኛዋ ነበረች።


       የፈረንሳይ ዲፕሎማት ሮቺ ሄሪኮርት እንደፃፈው ከ1500 እስከ 1700 የሚጠጉ ግመሎች የአገር ውስጥ ምርት ወደውጭ ያጓጉዙባት ነበር። በ1834 ዓ.ም እና 1835 ዓ.ም በአገራችን መጀመሪያ የሆነው የቀረጥ ውል የተፈረመው በአልዩ አምባ ገበያ መሠረት ነው። በከተማዋ ከፐርሽያ ( ኢራን) ፣ ከህንድና ከአረብ አገሮች የሚመጡ በርካታ የውጭ አገር ዜጎች ይኖሩባት እንደነበርም የተለያዩ ደራሲያን ጽፈውላታል።

   በዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ዘመን የቀረጥ መሥሪያ ቤት ሲከፈት በአልዩ አምባ የጉምሩክ ፅህፈት ቤት ሥራውን እንዲጀምር ተደርጎ ነበር። ስልክም ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ ከእንጦጦ እስከ አልዩ አምባ ድረስ መስመር ተዘርግቶለት የአካባቢው አዛውንቶች ይናገራሉ። እነዚሁ አባቶች አልዩ አምባ የተዳከመችው የባቡር ሐዲድ በከተማዋ ማለፍ ባለመቻሉና ወደ ድሬደዋ በመዛወሩ መሆኑን ያስረዳሉ ።  ዛሬ የአልዩ አምባ ገበያ አብዛኛዎቹን አርጎባዎች ይዞ የአፋርንና አማራ ብሔረሰቦችን ያገናኛል።

No comments:

Post a Comment