Monday, February 23, 2015

በቶኪዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ፆታ አሸነፉ፡፡



   በጃፓን በተካሄደው ዘጠነኛው የቶኪዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ ሆነዋል። በወንዶች ከ36ሺህ ተወዳዳሪዎች ቀዳሚ መሆን የቻለው እንደሻው ንጉሴ ውድድሩን ለማጠናቅቅ 2 ሰዓት፤ ከ06 ደቂቃ ከ00 ሰከንድ ወስዶበታል፡፡ አትሌት እንደሻው የሎንደን ኦሎምፒክ ባለድሉን ኡጋንዳዊ ስቴፈን ኪፕሮቲችና ያለፈውን ዓመት የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊ ኬንያዊ ዲክሰን ቹምባ በማስከተል ነው ውድድሩን ያጠናቀቀው።


  እንደሻው ንጉሴ እና ኪብሮቲች እስከ ውድድሩ ማጠናቀቂያ ብርቱ ፉክክር ማድርጋቸውን ዘገባው አትቷል፡፡ ኪፕሮቲች 33 ሴኮንድ ዘግይቶ በሁለተኛነት ሲያጠናቅቅ ቹምባ ሶስተኛ ሆኗል።



  የ26 ዓመቱ እንደሻው ከውድድሩ በኋላ ''ፈታኝ ውድድር ነበር ዝናብና ቅዝቃዜ ውደድሩን አስቸጋሪ አድርጎብኝ ነበር ሆኖም ውድድሩን አሸንፌያለሁ ህልሜ በቤጂንጉ የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ መሳተፍ ነው'' ብሏል፡፡


  በሴቶች ብርሃኔ ዲባባ 2 ሰዓት 23 ደቂቃ 15 ሴኮንድ አሸናፊ ስትሆን ኬንያዊቷ ሄላ ኪፕሮፕ ሁለተኛ የሎንደን ኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ ቲኪ ገላና ሶስተኛ ሆናለች።ብርሃኔ ዲባባ ደግሞ 2 ሰዓት፤ ከ23 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በሆነ ሰዓት የሴቶችን ምድብ አሸንፋለች፡፡ ኬኒያዊቷ ኪፕሮፕ ብርሃኔን ተክትላ ስትግባ፤ ኢትዮጵያዊቷ ቲኪ ገላና ደግሞ ውድድሩን ሶስትኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

   ዘጠኝ ዓመታትን ባስቆጠረው የቶኪዮ ማራቶን ታሪክ በሁለቱም ጾታዎች ከአንድ ሃገር የተገኙ አትሌቶች ሲያሸንፉ የእንደሻው እና የብርሃኔ ድል የመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ እንደሻው ንጉሴ እና ብርሃኔ ዲባባ ውድድሩን በማሸነፋቸው እያንዳንዳቸው 500ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ። የቶኪዮ ማራቶን በዓለማችን ታዋቂ ከሆኑት 6 የማራቶን ውድድሮች አንዱ ነው፡፡
                                               ምንጭ፡- IAAF

No comments:

Post a Comment