Thursday, November 21, 2013

በቅርቡ አሁን ካሉት ቴሌቪዥን ጣቢያቆች ውጪ ሌላ ሊከፈት እንደሚችል ተጠቆመ፡፡


    በቅርቡ ለግል የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ፍቃድ እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ልዑል ገብሩ መናገራቸው ተሰምቶል፡፡

 ከዚህ በተጨማሪም ዳይሬክተሩ፣መንግስት በጎ በጎውን ብቻ ሳይሆን ስህተት ሲሰራም የሚገስፀው የመገናኛ ብዙሀን ይፈልጋል፡፡ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ግን የመንግስትን በጎ ስራ ብቻ በመዘገብ ተጠምደዋል - ይህም በቂ ተግባር አይደለም…” ብለዋል፡፡

እውነትን ፈልፍለው የሚያወጡ ፕሮግራሞች የሉም፡፡ የኤፍ ኤም ሬድዮኖችም ከህብረተሰቡ ባህልጋ የሚጣረሱ፣ ሞራልና ስነምግባር የሌላቸው ዝግጅቶች ያቀርባሉ፣ በአልባሌ ዘገባዎች የአየር ሰዓትን ማባከንም ተጠናውቷቸዋል…” ይላሉ፡፡

                                                  ምንጭ ፡- ድሬ ቲዩብ

No comments:

Post a Comment