Sunday, November 3, 2013

ወይዘሮ ሙሉ ሰለሞን የሴት አመራር ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

 

 የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፉ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሙሉ ሰለሞን የአፍሪካና ህንድ የትብብር ጉባኤ የ2013 የሴት አመራር ሽልማትን አሸነፉ።

  ወይዘሮ ሙሉ ለዚህ ሽልማት የበቁት በተሰማሩበት የሙያ መስክ ላሳዩት የመሪነት ክህሎት እና ለሚኖሩበት ማህበረሰብ አስተዋፅኦ በማበርከታቸው ነው።  በመጪው ህዳር 18 ቀን 2006 ዓ.ም በሞሪሽየስ በሚደረገው 3ኛው የአፍሪካ ህንዳ የትብብር ጉባኤ ላይ ተገኝተው ሽልማታቸውን እንደሚረከቡ ታውቋል።

የአፍሪካ ሊደርሽፕ አዋርድ በአፍሪካ ህንድ የትብብር ጉባኤ ማዕቀፍ ውስጥ የተቋቋመ ሲሆን ሽልማቱ በተለይ በቢዝነስና የሰው ሃይል ልማት ዙሪያ የላቀ ድርሻ ላበረከቱ ግለሰቦችና የቢዝነስ ተቋማት የሚሰጥ ነው።

                                                   ምንጭ ፡-    ኤፍ ቢ ሲ

No comments:

Post a Comment