Wednesday, February 20, 2013

 ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ  ከፍተኛ ህመም ስላጋጠማቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ እና  ለአድናቂዎቻቸው የድረሱልኝ ጥሪ አቀረቡ ፡፡ ለጊዜው ከተለያዩ ታዋቂ የኢትዮጵያ አትሌቶች እሰከ ቅርብ ጊዜ ድረስ 700.000 ያህል  ገንዘብ ተሰባስቦላቸዋል ፡፡ ህክምናቸው ግን ከ1.3 ሚሊዮን ብር  በላይ ይፈጃል ተብሏል ፡፡  ስለዚህ እርሶዎም  ለኢትዮጵያ ባለውለታ  ለሆኑት  ለ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ ድጋፍዎትን ይለግሱ ፡፡
‹‹ ከገበሬ ቤተሰብ ነው የተወለድኩት ፡፡ አባቴ ኮስትሬ ሰብሬ አሸብር ይባላሉ፡ እናቴ ደግሞ እህተ ገብርኤል ደስታ ትባላለች፡፡ 5 ወንድሞች፣ 3 እህቶች አሉኝ፡፡ የተወለድኩት ተጉለትና ቡልጋ ሳሊት እንግዳ ዋሻ በተባለ ቦታ ነው›› ይላሉ፡፡ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ፡፡ ቤተሰቦቻቸው የቤተክርስቲያን ሰዎች በመሆናቸው ልጃቸው የድቁና ትምህርት ተምሮ በዲያቆንነት ቤተክርስቲያን እንዲያገለግል ነበር ምኞታቸው፡፡ ትንሹ ወልደመስቀል በ8 ዓመቱ ቄስ ትምህርት ቤት ገብቶ ዳዊት ደገመ፡፡ ከዚያም በትምህርት ተክኖ እንዲደቁን ወደ አዲስ አበባ ተላከ፡፡ ሆኖም በቤተሰብ ጭቅጭቅ የተነሳ ውጥኑ አልተሳካም፡፡ ይሁንና ልዩ ልዩ ውጣውረዶችን አልፈው  በርካታ ታዋቂ አትሌቶችን በማፍራት የኢትዮጵያ ስም በዓለም አደባባይ ዳግም እንዲጠራ በማድረግ ትልቅ ሚና ለመጫወት የቻሉ ብርቱ ሰው ናቸው፡፡ በስፖርተኞች፣ በስፖርት ቤተሰቡ አድናቆትና ተወዳጅነት ያተረፉት ዶ/ር ወልደመስቀል ሙያቸው በአንድ ቦታ ብቻ ተወሰነ ሳይሆን በእግር ኳስና በአትሌቲክስ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን በማሰልጠን በሁለት አንጋፋ ፌዴሬሽኖች የሙያ ግዴታቸውን የተወጡ ታላቅ ሰው ናቸው፡፡  ዶ/ር ወልደመስቀል ዛሬ ወደሚገኙበት ሙያ የመጡት አልመውና አመቻችተው ሳይሆን አውሮፕላን ውስጥ አቶ ይድነቃቸውን አግኝተው በመነጋገራቸው  በተፈጠረው አጋጣሚ ተጠቅመው እንደሆነ ከታሪካቸው መረዳት ይቻላል፡፡ ዶ/ር ወልደመስቀል ታዋቂ አትሌቶችን አሰልጥኖ ለጥሩ ደረጃ ማብቃት ብቻ ሳይሆን በእግር ኳሱም የቅ/ጊዮርጊስ አሰልጣኝ በነበሩበት ሰዓት በክለቡ ታዋቂ የነበሩትን እነ ስዩም አባተን፣ ተስፋዬና ዘሪሁንን የመሰሉ ተጨዋቾችን ከህፃናት ቡድኑ በማሳደግ ለትልቅ ደረጃ ማብቃት ችለዋል፡፡ ቅ/ጊዮርጊስ ከ5 ያልበለጡ ታዋቂ ተጨዋቾቹ ወደ አሜሪካ ሄደውበት በተተኪ ተጨዋቾች አደራጅተው ቡድኑን ለሻምፒዮና ከማብቃታቸውም ሌላ በአፍሪካ የክለብ ሻምፒዮናም በአሠልጣኝነት ሠርተዋል፡፡


No comments:

Post a Comment