“ለእኔ ራሱ ግርም ይለኛል ጭንቅላቴ ካሴት ማለት ነው ፣ አንዴ የተነገረኝን /የያዝኩትን/ ቶሎ አልረሳም በቃ ካሴት በሉኝ” እያሉ ጨዋታቸውን ሲያዥጎደጉዱት አፍ ያስከፍታሉ፡፡
የብሄራዊ ቲያትሯ መሪ ተዋናይ አርቲስት አስካለ አመነሸዋ ከትወናው አለም እስከተገለሉበት ጊዜ ድረስ “ሂሩት አባቷ ማን ነው” ን ጨምሮ ከ 40 በላይ ቲያትሮች ላይ ተሳትፈዋል፡፡ የድል አጥቢያ አርበኛ፣ ስነ-ስቅለት፣ አሸርቶስ ንጉስ፣ ቂመኛው ባህታዊ፣ ስራሽ ያውጣሽ፣ ታርቱፍ፣ ማንም ሰው፣ ደህና ሁኚ አራዳ፣ ደመ
መራራ፣ ንግስት ሳባ፣ አንድ አመት ካንድ ቀን፣ በህይወት ዙሪያ፣ ቴዎድሮስ፣ ስስታሙ መንጠቆ፣ አስቴር፣ ጎንደሬው ገ/ማሪያም፣ አወናባጅ ደብተራ፣ ምኞቴ፣ የሺ፣ እኝ ብዬ መጣሁ፣ ለሰው ሞት አነሰው፣ ኦቴሎ፣ የበጋ ሌሊት ራዕይ፣ የከተማው ባላገር፣ ጠያቂ እና የአዛውንቶች ክበብን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ነጋሽ ገ/ማሪያም የተደረሰው የአዛውንቶች ክበብ የመጨረሻ ስራቸው እንደሆነም ይናገራሉ፡፡

የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ ….. አይደል ያለው ቴዲ አፍሮ በዘፈኑ፡፡ እኛም ቀደምቶቻችንን እናስብ፤ እነሱንም እንጠይቅ፣ እንመርምር ብዙ ቁምነገሮችንም እናገኛለንና…….
No comments:
Post a Comment