በንፋስ ስልክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለአራት ዓመታት ያስተማሩት ዶ/ር ለገሰ ለ40 ዓመታት ያህል በመምህርነትና በተመራማሪነት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አገልግለዋል፡፡ዶ/ር ለገሰ ወትሮ አስትሮኖሚ/አስትሮ- ፊዚክስ ምርምር የሚታወቁ እና አዳዲስ ፅንሰ - ሀሳቦችን ያበረከቱ ታላቅ ሰው ነበሩ ብሏል የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ መግለጫ፡፡
ዶ/ር ለገሰ ወትሮ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 “የህዋ ሳይንስ” የተሰኘ ፕሮግራም በማዘጋጀት ለአድማጮች ስለ ህዋ ሳይንስ ሰፊ ግንዛቤ ይሰጡም ነበር፡፡ በተወለዱ በ67 ዓመታቸው ያረፉት ዶ/ር ለገሰ የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡ የዶ/ር ለገሰ ወትሮ ስርዓተ ቀብር ሚያዝያ
20/2009 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በጴጥሮስ መካነ መቃብር ይፈጸማል ሲል አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አስታውቋል፡፡
ለቤተሰቦቻቸው
እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን!!!
No comments:
Post a Comment