ተወልደ ገብረማሪያም የ2013 የአየር መንገድ ስተራቴጂ ሽልማትን አሸነፉ
ሃምሌ 11 ፣ 2005የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም አየር መንገዱ ቀጠናዊ ትስስሩን በማስፋት ለተጫወቱት ሚና የአየር መንገድ ክልላዊ አመራር ሽልማትን አሸነፉ፡፡
ዋና ስራ አስፈፃሚው ሽልማቱን በአለም አቀፍ አየር በረራ ዘገባ ከሚሰራውና ቀዳሚ የአቬየሽን መፅሄት ከሆነው ኤር ላይን ቢዝነስ ተቀብለዋል፡፡ሽልማቱ አንዱን የአለማችን ክፍል ከሌላው ጋር በአየር ትራንስፖርት ጠንካራ ትስስር እንዲኖረው አመራር ለሰጡ የሚበረከት ነው፡፡
ሽልማቱ ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑት የአየር መንገዱ ሰራተኞች ታታሪነትና ጠንክሮ የመስራት ውጤት መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ሽልማቱን በተቀበሉበት ወቅት ተናግረዋል፡፡ ለድርጅቱ ሰራተኞች ምስጋናቸውን ያቀረቡት ዋና ስራ አስፈጻሚው ፥ ሽልማቱ አየር መንገዱ እ.ኤ.አ በ2025 ለማሳካት የወጠነው ራዕይ ስኬታማ እየሆነ መምጣቱን አመላካች እንደሆነም ገልፀዋል፡፡
አየር መንገዱ በ2025 ፍኖተ ካርታው 7 ራሳቸውን የቻሉ የስራ ክፍሎችን በማቋቋም በአመት 10 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የማስገኘት ራዕይ ይዞ እየሰራ መሆኑን ከአየር መንገዱ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ምንጭ ፡- ፋና ኤፍ ኤም 98.1
No comments:
Post a Comment