የ12ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆነ
ሃምሌ 12 ፣ 2005
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተናን ከወሰዱ አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ከ350 በላይ ነጥብ ማስመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ ተናገረ ።
የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን ዱሬሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ፥ የተመዘገበው ውጤት ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ7 በመቶ ብልጫ አለው። በዘንድሮው ፈተና ከፍተኛ ውጤቶች የተመዘገቡት በመንግስት ትምህርት ቤቶች ሲሆን ፥ ከአምቦ ከተማ 637 በመሆን የተመዘገበው ደግሞ ከፍተኛው ውጤት ነው።
በፈተናው ተመሳሳይ ውጤቶች ያልተመዘገቡ ሲሆን ፥ ይህም ከኩረጃ የጸዳ የፈተና ስርአት መኖሩን እንደሚያሳይ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የዩኒቨርሲቲዎች መግቢያ ነጥብ በቅርቡ ይገለጻል ያሉት ዳይሬክተሩ ፥ ተማሪዎች ያመጡትን ነጥብ www.nae.gov.et ላይ እንዲሁም በሞባይል ስልኮቻቸው አማካኝነት በጽሁፍ መልዕክት መላኪያ በመግባት RTW ብለው በመጻፍ የፈተና ቁጥራቸውን በማስገባት እና በ8181 የጽሁፍ መልዕክት በመላክ ማየት እንደሚችሉም ነው የተናገሩት።
Source : - Fana Fm 98.1
No comments:
Post a Comment