በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ውስጥ የምትገኘው ጓሳ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 180 ኪሜ ላይ ትገኛለች፡፡ ከባሕር ወለል በላይ በ3417 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘዋን ከፍተኛ ደጋማ ቦታ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመሆን እየሠራ የሚገኘው ፍራንክፈርት ዚኦሎጂካል ሶሳይቲ ነው፡፡ ተቋሙ በማኅበረሰብ ተኮር የቱሪዝም አካባቢ ጥበቃ ላይ በመሥራት ይገኛል፡፡ የፍራንክፈር ዚኦሉጂካል ሶሳይቲ የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ዘላለም ተፈራ እንደተናገሩት፣ መጠሪያ ስሟን ‹‹ጓሳ›› ከሚባል ተክል ያገኘችው ጓሳ ብርቅዬ አዕዋፋትና የዱር እንስሳት የሚገኙባት፣ የመንዝ ጥንታዊና ባህላዊ የቤት አሠራር ሥነ ሕንፃ የሚታይባት፣ ከጓሳም ሆነ ከሌላ ቁስ የሚሠሩ ዕደ ጥበባት የሚገኝባት ናት፡፡ የጓሳ አካባቢ በኢትዮጵያ ብቻ ከሚገኙ አጥቢ እንስሳት 23 በመቶ የሚሆኑት የሚገኙበት ብርቅዬውን የኢትዮጵያ ተኩላ በቅርበት ለማየት የሚቻልበት፣ የጭላዳ ዝንጀሮም መናኸሪያ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት 861 የወፎች ዝርያዎች 114ቱ ይገኙበታል፡፡ ፍራንክፈርት ዚኦሎጂካል ሶሳይቲ የአካባቢው ኅብረተሰብ ባሉት የመስህብ ቦታዎች ተጠቃሚ የሚሆንበትን ቦታውም የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን የጓሳ ማኅበረሰብ ሎጅ በስፍራው በማቋቋም እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ጓሳ የሚገኝበት የመንዝ- ጌራ ወረዳ ከተማ የሆነው መሐል ሜዳ ከአዲስ አበባ 282 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ከአዲስ አበባ ወደ ጓሳ ሲኬድ መተላለፊያው መዳረሻው ላይ በምትገኘው ይገም መንደር (ከጓሳ ሎጅ 12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ) በታሪካዊው አርባራ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ያልፈረሱ አጽሞችም ይታዩበታል፡፡ ‹‹ካለን የተፈጥሮ መስህብ ሀብት በተጨማሪ ትሁትና እንግዳ ተቀባይ ሕዝብ፣ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል የመረጃ ማዕከልና ሎጅ ፣ ለመጓጓዣ የሚጠቅሙ በቅሎና ፈረስ፣ የጎብኝዎችን ፍላጎት ሊያሟሉ የሚችሉ በአካባቢው ቁሳቁስ የተሠሩ የዕደ ጥበብ ውጤቶች አሉንና ኑና ጎብኙን፡፡
No comments:
Post a Comment