አርቲስት 50 ዓለቃ ሸዋንዳኝ ወልደየስ ተወዛዋዥ ፣ የውዝዋዜ አሰልጣኝ ፣ ግጥም እና ዜማ ደራሲ ፣ ድምፃዊ እና የክብር ዘበኛ አባል ሲሆኑ በተለይ “ጃፓኗን ወድጄ” በተሰኘው የክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ ስራ ይታወቃሉ፡፡ አርቲስት 50 ዓለቃ ሸዋንዳኝ ወልደየስ ብሩ በሰሜን ሸዋ ቡልጋ አውራጃ በ1926 ተወለዱ፡፡ ከዛም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት እድገታቸውና የልጅነት ጊዜያቸውን ላምበረት ሾላ አካባቢ አሳልፈዋል፡፡
በራሳቸው ድምፅ ፣ ግጥም እና ዜማዎችን ደርሰው ከተጫወቷቸው
ሙዚቃዎች ውስጥ ፡- ሰው መመልከትሽ ይቅር (እኔ እበቃሻለሁ) ፣ አዲስ አበባ የተዋብሽው ፣ ስራ አትፍቺ ፣ ፍቅርን አታውቂ እና
ወይ አዲስ አበባ የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ “እንዋደድ ነበር” የሚል ሙዚቃን ከድምፃዊ ተዘራ ሀይለሚካኤል ጋር የተጫወቱ ሲሆን
ለጥላሁን ገሰሰ - ስትሄድ ስከተላት እና ጃፓኗን ወድጄ ፣
ለብዙነሽ በቀለ - እንዲህ ነው ጋብቻ (የማይሞት ጋብቻ) ፣ ለመሀሙድ አህመድ - ፍቅር በዘበዘኝ የሚሉ ስራዎችን ስጥተዋል፡፡ የራሳቸውም
ሆነ ለሌሎች ድምፃውያን የሰጧቸው አብዛኞቹ ዘፈኖች እውነተኛ እና የራሳቸው ታሪኮች ናቸው፡፡ “ጃፓኗን ወድጄ”ም የ50 ዓለቃ
ሸዋንዳኝ
ወልደየስ
እውነታኛ ታሪክ እና ዜማውም የራሳቸው ድርሰት ነው፡፡
በክብር ዘበኛ ሙዚቃ ኦርኬስትራ ዉስጥ ተቀጥረዉ እያገለገሉ እያለ በ1954 ዓ.ም ከወ/ሮ የሺእመቤት ወለደማሪያም ጋር ጋብቻ መስርተዉ 8 ወንዶችና 3 ሴቶች በድምሩ 11 ልጆችን አፍርተዋል፤14 የልጅ ልጆችን እና 2 የልጅ ልጅ ልጆችን አይተዋል፡፡ በክብር ዘበኛ ውስጥ ከ30 አመት በላይ ያገለገሉት አርቲስት 50 ዓለቃ ሸዋንዳኝ ከ60 አመታት በላይ የተሻገረው ታዳራቸው /ጋብቻቸው/ በክብር ዘበኛ ሙዚቃ ክፍል በእነ ጥላሁን ገሰሰ ፣ አበበ ተሰማ ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ ተዘራ ሃይለሚካኤል እና ሌሎች የክብር ዘበኛ አባላት ድምቆላቸዋል፡፡ ሚዜዎቻቸው እነ ኮለኔል ሳህሌ ደጋጎ ፣ ተካልኝ ፀጋ እና አሰፋ ሀይሌ የተባሉ የክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ አባላት እንደነበሩም በህይወት በነበሩ ጊዜ አጫውተውናል፡፡
የባለብዙ ታሪክ
ባለቤት እና
ሁለገብ የጥበብ ሰው የሆኑት አርቲስት
50 ዓለቃ
ሸዋንዳኝ
ወልደየስ
በ1974
ከክብር
ዘበኛ
ሙዚቃ
ኦርኬስትራ
ጡረታ
ከወጡ
በኋላ
በግላቸዉ
የራሳቸዉን
ስራ
እየሰሩ
ህይወታቸዉን
ሲመሩ
ቆይተዋል፡፡
አርቲስት
50 ዓለቃ
ሸዋንዳኝ
ወልደየስ
በተወለዱ
በ88
ዓመታቸዉ
ትናንት
ሚያዝያ
26 ቀን
2014 ዓ.ም
ምሽት
3 ሰዓት
አካባቢ
ህይወታቸዉ
ማለፉንና
የቀብራቸዉ
ስነ ስርዓትም በነገዉ እለት/28/8/2014ዓ.ም በአዲስ
አበባ
የካ
ሚካኤል ቤተ
ክርስቲያን
ከቀኑ
9፡00
እንደሚፈፀም
ልጃቸዉ
እየሩሳሌም
ሽዋንዳኝ
ገልፀውልናል፡፡
ለእሳቸው እረፍተ ነፍስን ፤ ለቤተሰቦቻቸው ፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና አድናቂዎቻቸው ደግሞ መፅናናትን እንመኛለን፡፡