Monday, August 15, 2016

12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ



  የ12 ክፍል አገራቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሪክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር አስታውቀዋል፡፡ ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ዌብሳይት www.neaea.gov.et ላይ Student result የሚለው ቦታ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ማየት ይቻላሉ፡፡ ውጤት ለማየት ሌላኛው አማራጭ ደግሞ በነፃ አጭር የፅሁፍ መልክት 8181 ላይ RTW ብለው በመፃፍ  እና ክፍተት በመተው (ስፔስ በማድረግ) የመለያ ቁጥራቸውን አስገብተው በመላክ ማወቅ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

  የዘንድሮው 12 ክፍል መግቢያ ፈተና በመሰረቁ ምክንያት በተሰጠው ልዩ ትኩረት ቀን ከለሊት በመሰራቱ  እና ኤጀንሲው ተጨማሪ 10 የማረሚያ ማሽኖች ገዝቶ ወደ ስራ በማስገባቱ ውጤቱን በአፋጣኝ ለማውጣት መቻሉን የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሺፋ ገልፀዋል፡፡

 ብሄራዊ ፈተናውን 246 ሺህ 570 ተፈታኞች የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 50 በመቶዎቹ 350 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። 106 ተፈታኞች ደግሞ 600 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 21ዱ ሴቶች ናቸው። ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥቡ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆንም ኤጀንሲው አስታውቋል።
  10 ክፍል ውጤትም ከሐምሌ 15 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ ይፋ እንደሚደረግም ለማወቅ ተችሏል፡፡ 10 ክፍል ውጤት 12ኞቹ የዘገየው የተፈታኞቹ ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ በመሆኑ ለማረም የበለጠ ጊዜ በመፍጀቱ እንደሆነ ነው አቶ ረዲ ያስታወቁት፡፡

No comments:

Post a Comment