Sunday, August 21, 2016

የዘመን መለወጫ ዋዜማ … ሂሩት በቀለ …ትውስታ !!!


  ቀደም ባለው ጊዜ በሙዚቃው አለም የተሠማራ ሰው አዝማሪ ስለሚባል ብዙዎች ወደ ሙያው ለመግባት ይቸገሩ ነበር፡፡ ከቤተሰብም ውስጥ ልጆቻቸው አዝማሪ እንዳይባሉ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያደርጉ ነበር፡፡ ድምፃዊት ሂሩት በቀለም ይህንን ፍራቻ ቤተሰቦቿ ሳያውቁ 1 አመት ያህል ሠርታለች፡፡

  በ1951 . ተፈትና ምድር ጦር ኦርኬስትራ የተቀላቀለችው ሂሩት ለፈተና የተወዳዳረችበት ዘፈኗየሀር ሸረሪትይሰኛል፡፡ ይህንንም ዘፈን ከምድር ጦር ኦርኬስትራ ጋር በመሆን ለአዲስ አመት /ዘመን መለወጫ በዓል/ በብሄራዊ ትያትር መድረክ ላይ ተጫውታለች ይሁንና ከማፈሯ እና መደንገጧ የተነሳ ዘፈኑን ሳትጨርሰው ከመድረክ ወርዳለች፡፡ በኋላ ግን አሰገደች ካሳ ዘፈኑን እንደሷ አስመስላ ለታዳሚው ለመጫወት ሞክራለች፡፡

  በምድር ጦር ብዙም ሳትቆይ 1952 . ፓሊስ ሰራዊት ሙዚቃ ክፍል ገብታ በጡረታ እስከተገለለችበት ጊዜ ድረስ ለ30 ዓመትት ያህል አገልግላለች፡፡ አስገራሚ በሆነ ሁኔታም ፖሊስ ሰራዊት ሂሩትን ከምድር ጦር አስኮብልሏል፡፡ በጊዜውም ምድር ጦር ይከፈላት የነበረው ደሞዟ 60 ብር ሲሆን በፖሊስ ኦርኬስትራ 100 ብር አድጎላት ነበር፡፡ ከዚያን በኋላ በየዘመን መለወጫው ዋዜማ የበዓል ስራዎቿን በማቅረብ ከህዝብ አድናቆት እና አክብሮትን አግኝታለች፡፡ በፓሊስ ቆይታዋም በርካታ ካሰቶችን ሠርታለች፡፡ 


  ድምፃዊት ሂሩት በቀለ በግል ከሰራቻቸው ሙዚቃዎች ባሻገርም በጋራ የተጫወተቻቸው ጥቂት የማይባሉ ሙዚቃዎች አሏት፡፡ በአጠቃላይ በቆይታዎ ከምድር ጦር እና ፓሊስ ኦርኬስትራ እንዲሁም ዋልያስ ፣ ሮሃ እና ዳህላስ ባንዶች ጋር ስራዎቿን አቅርባለች፡፡ እዚሁ መዲናችን አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ድምፃዊት ሂሩት በቀለ አሁን ራሷን ከሙዚቃው አለም አግልላ ወደ መንፈሳዊ አለም ገብታለች ፡፡ 

No comments:

Post a Comment