Thursday, March 17, 2016

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ - መዛብትና ቤተ - መጻሕፍት ኤጀንሲ (ወመዘክር)....




ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍትየሕህብ ቤተመጻሕፍት ወመዘክርበሚል ስያሜ 1936 . በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ የተከፈተ ሲሆን አገልግሎት መስጠት የጀመረውም ንጉሱ ባበረከቱት 200 በላይ የመጻሕፍት ስጦታ ነው፡፡
1958 . በተደረገው የቤተመጻሕፍት መዋቅር ለውጥ ብሔራዊ ቤተመጻሕፍት የሚል ስያሜ ይዞ በጥንታዊ ቅርሶች አስተዳደር ሥር እንዲሠራ ተደረገ፣ 1967 . በመጀመሪያ ደረጃ ተዋቅሮ ሥራውን ቀጠለ፡፡
1968 . በአዋጅ ቁጥር 50/68 ለባህልና ስፖርት ጉዳይ / በሀገር ውስጥ ከሚታተሙ ማናቸውም ህትመቶች ሶስት ሶስት ቅጂዎችን እንዲረከብ በመንግስት የተሰጠውን ሥልጣን ቤተ-መጻሕፍቱ እንድያስፈጽም ውክልና አገኘ፡፡


1972 . ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት መምሪያ ተብሎ ስራውን እንድያከናውን ተደረገ፣ 1986 . በተደረገ የመዋቅር ለውጥ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት የሚል ስያሜ ይዞ እንድሠራ ተደረገ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 179/91 በሀገሪቱ የሚገኙ መዛግብትን መጻሕፍትንና መሠል ጽሁፎችን በአንድ ማዕከል ስር በማሰባሰብና በማደራጀት የሀገሪቱን የመረጃ አገልግሎት በተቀናጀ ሁኔታ መምራት የሚያስችለውን ህጋዊ ሰውነት አገኘ፡፡
1998 . የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባፀደቀው አዋጅ ቁጥር 471/98 የአስፈጻሚ /ቤቶች ስያሜ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት - ኤጀንሲ በሚል መጠሪያ እንዲለወጥ ተደርጎ የተጣለበትን ኃላፍነት በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

No comments:

Post a Comment