Saturday, February 20, 2016

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በስፔን ካታላን በተደረገ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አሸነፈች።


  አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ይህን ውድድር ሁለተኛውን የዓለም ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ነው ያሸነፈችው፡፡ አትሌቷ ይህንን ውጤት ያስመዘገበችው በአንድ ማይል የቤት ውስጥ ውድር የዓለምን ክበረ ወሰን ከሰበረች ከሁለት ቀን በኋላ ነው። ገንዘቤ ትናንት ምሽት በስፔን ካታላን በተካሄደው የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ሁለት የአገሯን ልጆች አስከትላ ውድድሩን በበላይነት አጠናቃለች። ውድድሩን ለማጠናቀቅም 8 ደቂቃ ከ22 ሴኮንድ ከ50 ማይክሮ ሴኮንድ ፈጅቶባታል።
   ይህ ሰዓት በዓለም ሪከርድነት ካስመዘገበችው 8 ደቂቃ 16 ሰከንድ 60 ማክሮሰከንድ ቀጥሎ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ነው። አትሌት ገለቴ ቡርቃ በ8 ደቂቃ 33 ሰከንድ 76 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ ስትሆን አትሌት ጎይቶም ገብረ ስላሴ ደግሞ ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።
  በ2015 በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር  ''የዓለም ምርጥ ሴት አትሌት'' ትብላ የተሸለመችው ገንዘቤ የ2016 ውድድሯን የአንድ ማይል የዓለም  ክብር ወሰንን በመስበር ጀምራለች። ገንዘቤ እስካሁን ከሰበረቻቸው የዓለም ክብረወሰኖች አራቱ በቤት ውስጥ ውድድር ሲሆን አንድ ክብረወሰንም ከቤት ውጭ አሻሽላለች። ከብረወሰን ካስመዘገበችባቸው ውድድሮች ሶስቱን ያስመዘገበችው በስዊዲን መሆኑ ይታወቃል።

                                                 ምንጭ፦ ኢዜአ

No comments:

Post a Comment