Friday, April 18, 2014

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 2.8 ቢሊየን ዶላር በሆነ ወጪ አምስት የማዳበሪያ ፋብሪካዎችን እየገነባች ነው፡፡


      የኢንዱስትሪ ሚንስትር እሮብ ዕለት እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 2.8 ቢሊየን ዶላር በሆነ ወጪ አምስት የማዳበሪያ ፋብሪካዎችን እየገነባች ትገኛለች፡፡ አምስቱም ፋብሪካዎች ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ አቅጣጫ 330 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ባለው የያዩ አካባቢ የሚገኙ ሲሆን እያንዳንዱ ፋብሪካም በዓመት 300 000 ቶን ማዳበሪያ የማምረት ብቃት አለው ተብሏል፡፡

  ኢትዮጵያ 103.3 ሚሊየን ዶላር በላይ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣ ሲሆን .. 2017 ስራቸውን ይጀምራሉ የተባሉት እነዚህ ፋብሪካዎች ከውጭ የሚገባውን የማዳበሪያ አቅርቦት በተወሰነ መልኩ ከመሸፈንም በላይ ማዳበሪያዎቹ ከውጭ በሚገቡበት ወቅት በወደብ አካባቢ የሚፈጠረውን መጣበብ ያስቀራል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

   ፋብሪካዎቹ የተተከሉበት ቦታ የተመረጠው በቦታው የከሰል ድንጋይና ሌሎችም የፋብሪካው ጥሬ እቃዎች በአካባቢው በመኖራቸው ሳቢያ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በዘርፉ መንግስት ቢገባበትም ወደፊት ግን የግል ባለሀብቶችም ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

No comments:

Post a Comment