የዘፈን ግጥም እና ዜማ ደራሲ ፤ አሳታሚ እና አከፋፋይ እንዲሁም የቀድሞ ኢትዮጵያ አይዶል እና የኮካ ኮላ ሱፐር ስታር ዳኛ ነው ፤ የአስጎብኚ ድርጅት ከፍቶም እየሰራ ይገኛል፤ ሁለገቡ ባለሙያ ዘላለም መኩሪያ፡፡
ስለ ስራዎቹ በጥቂቱ እነሆ….
1. መሀሙድ አህመድ - ብክንክን ፣ መውደድ አዛዥ ነው
2. አለማየሁ እሸቴ - ደገኛ ነች ፣ ልሂድ ልወዝወዘው
3. ኤፍሬም ታምሩ - አደላድዬው ፣ እስከ መቼም አልረሳው ፣ መውደድ/ፍቅር በኔ ፀንቶ
4. ፀጋዬ እሽቱ - ክፉ አልምደሽኝ/እናት ወደር የላት/
5. አረጋኽኝ ወራሽ - የአምባው ዳኛ
6. ኬኔዲ መንገሻ - ዘወርዋራ (የመጀመሪያ ስራው ነው)
7. ሰርጉአለም ተገኝ - በምን ቃል ፣ አሆበል
8. ማዲንጎ አፈወርቅ - አይደረግም ፣ ስያሜ አጣሁላት
9. በዛወርቅ አስፋው - መውደድ ካኮራህ /ልቤን ታዘብኩት/
10. ማርታ አሻጋሪ - እምቢ እምቢ ፣ ግልፅ ነው ስሜቴ ፣ የልጅ ነገርማ እና ሌሎችም በዛ ያሉት የእሱ ስራዎች ናቸው፡፡
11. ተሾመ አሰግድ - እረ እንዲያው በረታ
12. ውብሸት ፍሰሃ - መካር የላት ምነው
13. ነፃነት መለሰ- ያለስንብት፣ ያይኔራብ ፣ ይወስደኛል
14. ኩኩ ሰብስቤ - አከራርመኝ - ከውብሽት ጋር በመሆን
15. ሀይልዬ ታደሰ - አንቺን ይዞ (አንቺ የሌለሽበት)
16. ገረመው አስፋ - በይ እንዳሻሽ
17. ዳዊት መለሰ -
18. ፋሲካ ዲመትሪ -
19. ኤልሳቤጥ ተሾመ - እፈራለሁ
20. ለኢትዮጵያ አይዶል ተወዳዳሪዎች (ለዳንኤል እና ሱራፌል)
# በዜማ ድርሰት የተሳተፈባቸው የባህል ስራዎች
1. ታደሰ አለሙ - ሚሻ ሚሾ
2. የሺመቤት ዱባለ - አሳበለው (አልበም)
3. የኔጌጥ ፋንታሁን - ምን ይላል ጎንደር ሲከፋው : የልቤ ሌባ ቀማኛ (የዳኛ ዳኛ)
4. መሰሉ ፋንታሁን - አይንዬ
5. ማናሊሞሽ ዲቦ - አሳበለው ፣ አለሁ በለኝ
6. እያዩ ማንያዝዋል - ከብዙ በጥቂቱ የእሱን የዜማ እና ግጥም ድርሰቶች የተጫወቱ ድምፃውያን ናቸው፡፡
# ህብረ ዜማዎች
- የመከላከያ ሰራዊት መዝሙር ፣ የአፍሪካ ህብረት ፣ የኮፒ ራይት - (ይስማን ወገን ይስማን) ፣ የኢትዮጵያ አይዶል አሸናፊዎች ፣ የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ፣ የአርበኞች በዓል ፣ ለአትሌቶች - የሲድኒው ሰራዊት እና የደል ብስራት (ለመከላከያ የተሰራ) ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
# በበሙዚቃ ህትመት እና ማከፋፈል ደግሞ
1. አሳበለው - መሰሉ፣ ማናሊሞሽ እና የኔጌጥ
2. ስያሜ አጣሁላት - ማዲንጎ አፈወርቅ
3. እድሜዬን በሙሉ - አብርሽ ዘጌት
4. ባንቺው መጀን - ደርብ ዘነብ
5. የኔ ድሃ - ነዋይ ደበበ
6. ሰም እና ወርቅ - ጂጂ(እጅጋየሁ ሽባባው)
7. ባስረሳኝ - ብፅአት ስዩም
8. የሰላም ይሁን - አስፋው ፅጌ
9. ሚሻ ሚሾ - ታደሰ አለሙ ፣ እነዚህና ሌሎች ስራዎችን በማሳተም በሙዚቃው ውስጥ አሻራውን አኑሯል፡፡