በሀገር ፍቅር ፣ በህፃናት እና ወጣቶች ፣ ሜጋ ኪነ ጥበባት ፣ ብሄራዊ ትያትር እና አሁን እየሰራች ያለችበት የአ.አ ትያትር እና ባህል አዳራሽ(ማዘጋጃ ቤት) ልዩ ልዩ ትያትሮችን ሰርታለች፡፡ ለአብነትም :-
2. ሜጋ ኪነ ጥበብ - (አብሮ አደግ እና ይግባኝ...)
3. ብሄራዊ ትያትር - (የ13 ወር ፀጋ...)
4. ትያትር እና ባህል አዳራሽ - (እድል 20 ፣ ጥቁሩ መናኝ ፣ ፍላጎቶቼ እና ነብይ ዤሮ...)
5. ህፃናት እና ወጣቶች (የጠፋችው ልዕልት ፣ ብርቅዬዋ ዶሮ ፣ ሁለቱ ወንድማማቾች ፣ ሰኞ ማክሰኞ ፣ አምስቱ ጣቶች ፣ የተቀደደው ተራራ ፣ ዱዱ ...)
6. እምቢልታ ሲኒማ - (ጠቋሪት ፣ የዋሻዋ እመቤት ፣ መሃረቤ 1 እና 2 ፣ አብቹ ፣ ቹቹ ፣ ቶፊዬ ፣ ሁለቱ አይጦች እና ነይ እርግብ አሞራ...)
በቴሌቭዥን ስራዎችም:- በኢቢሲ - ቤቶች ተከታታይ ድራማ ፣ በአዲስ ቲቪ - የተለያዩ ድራማዎች እና ስፖቶች ፣ በኢቢኤስ - ልዩ ልዩ የበዓል ስራዎች (4 ቤት እና የኤዞፕ ምድር) ፣ አርትስ ቲቪ - አዲስ ድባብ(የልጆች ፕሮግራም) እና አሻም ቲቪ - ንፁህ ነፍሶች (የልጆች ፕሮግራም) የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
“ያልወረደ ሸክምን” ጨምሮ 10 የሚጠጉ የሬዲዮ ድራማዎችንም ሰርታለች ፡፡ ጥቁር እና ነጭ ፣ 79 ፣ አዲስ ሙሽራ - 2 ፣ ግልባጭ ፣ሴት እና አሜሪካ ፣ ላይ እና ታች እና ካምፓስ ከሰራቻቸው ፊልሞች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ከአ.አ ዩኒበርስቲ በትያትር ሙያ የመጀመሪያ ዲግሪዋን አግኝታለች፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በህክም ሙያ በነርሲንግ ተመርቃለች፡፡ የሁለት ወንድ ልጆች እናት የሆነችው አርቲስት አስታውሺኝ በነጋ ቀልድ እና ጨዋታ አዋቂ ናት፡፡ ብዙም ስላልተነገረላት እና ስላልተዘመረላት አርቲስት አስታውሺኝ በነጋ
ከብዙ በጥቂቱ እኔ ይህንን አካፈልኳችሁ፣ እናንተ ደግሞ በማስፋት እና በማዳበር ተጨማሪ መረጃዎችን ልታጋሩኝ ትችላላችሁ፡፡
ለሁለገቧ ባለሙያ አርቲስት አስታውሺኝ በነጋ እድሜ እና ጤናን እመኛለሁ፤
በሌላ ጊዜ በሌላ እንግዳ እንገናኛለን፡፡ ቸር ይግጠመን !!!