Wednesday, March 5, 2014

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ አረፉ


 የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድርና የኦህዴድ የቀድሞው ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ አቶምሳ አረፉ። 
አቶ አለማየሁ አቶምሳ በታይላንድ ባንኮክ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ 45 አመታቸው ነው ዛሬ ሌሊት ሰባት ሰዓት ላይ ያረፉት። አቶ አለማየሁ ከየካቲት 9 ቀን 2006 ጀምሮ በባንኮክ ህክምናቸውን ሲከታተሉ እንደቆዩ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው። በምስራቅ ወለጋ ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው አቶ አቶምሳ ሚጃ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አየለች ብሩ 1961 ዓ.ም ነው የተወለዱት። የኦህዴድ ማዕከላዊ  ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫም፥ ላለፉት 24  ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ እና መላው የአገሪቱ ህዝቦች  ዛሬ ለደረሱበት የሰላም፣ የዴሞክራሲና የልማት ተጠቃሚነት እንዲበቁ በቁርጠኝነት የታገሉ ነባር  ታጋይ ነበሩ ብሏል።
   
  1981 ዓ.ም የደርግን ስርዓት ለመገርሰስ ሲካሄድ የነበረውን የትጥቅ ትግል ተቀላቅለዋል። 1988 እስከ 1994 ድረስም የኦህዴድ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት እና የድርጅቱ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ በመሆን አገልግለዋል። 2002 ዓ.ም ጀምሮ የኦህዴድ ሊቀመንበር ሆነው፥ 2003 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ሰርተዋል።

No comments:

Post a Comment