Sunday, July 14, 2013

በቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ ሩዋንዳን አሸነፉ


              ሃምሌ 7 ፣ 2005

    ቻን በሀገር ውስጥ የሊግ ውድድር የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በሚቀጥለው አመት በደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው 3ኛው የቻን አፍሪካ ዋንጫ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ።
     የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደቡብ አፍሪካ ላይ በድጋሚ ለመገኘት የማጣሪያ ጨዋታዎቹን እያደረገ ሲሆን ፥ ቡድኑ በቅድመ ማጣሪያ ከኤርትራ ጋር ተደልድሎ ኤርትራ ራስዋን በማግለሏ  ምክንያት በፎርፌ ለቀጣዩ ጨዋታ አልፏል።

      ዛሬ ከቀኑ 10 ሰአት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የአንደኛ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታ ዋልያዎቹ  የሩዋንዳ አቻውን በአስራት መገርሳ ጎል 1 ለ 0 አሸንፈዋል ።

No comments:

Post a Comment