በምድር ጦር ብዙም ሳትቆይ በ1952 ዓ.ም ፓሊስ ሰራዊት ሙዚቃ ክፍል ገብታ በጡረታ እስከተገለለችበት ጊዜ ድረስ ለ30 ዓመትት ያህል አገልግላለች፡፡ አስገራሚ በሆነ ሁኔታም ፖሊስ ሰራዊት ሂሩትን ከምድር
ጦር አስኮብልሏል፡፡ በጊዜውም ምድር ጦር ይከፈላት የነበረው ደሞዟ 60 ብር ሲሆን በፖሊስ ኦርኬስትራ 100 ብር አድጎላት ነበር፡፡
ከዚያን በኋላ በየዘመን መለወጫው ዋዜማ የበዓል ስራዎቿን በማቅረብ ከህዝብ አድናቆት እና አክብሮትን አግኝታለች፡፡ በፓሊስ ቆይታዋም በርካታ ካሰቶችን ሠርታለች፡፡
ድምፃዊት ሂሩት በቀለ በግል ከሰራቻቸው ሙዚቃዎች ባሻገርም በጋራ የተጫወተቻቸው ጥቂት የማይባሉ ሙዚቃዎች አሏት፡፡ በአጠቃላይ በቆይታዎ ከምድር ጦር እና ፓሊስ ኦርኬስትራ እንዲሁም ዋልያስ ፣ ሮሃ እና ዳህላስ ባንዶች ጋር ስራዎቿን አቅርባለች፡፡ እዚሁ መዲናችን አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ድምፃዊት ሂሩት በቀለ አሁን ራሷን ከሙዚቃው አለም አግልላ ወደ መንፈሳዊ አለም
ገብታለች ፡፡